የድቅል በቆሎ ዘር እጥረትን ለማቃለል የቀጥታ የዘር ግብይት ሥርዓት መመሪያ ማፅደቁን የግብርና ሚኒስቴር አስታወቀ

© telegram sputnik_ethiopiaየድቅል በቆሎ ዘር እጥረትን ለማቃለል የቀጥታ የዘር ግብይት ሥርዓት መመሪያ ማፅደቁን የግብርና ሚኒስቴር አስታወቀ
የድቅል በቆሎ ዘር እጥረትን ለማቃለል የቀጥታ የዘር ግብይት ሥርዓት መመሪያ ማፅደቁን የግብርና ሚኒስቴር አስታወቀ - Sputnik አፍሪካ, 1920, 13.07.2026
ሰብስክራይብ

የድቅል በቆሎ ዘር እጥረትን ለማቃለል የቀጥታ የዘር ግብይት ሥርዓት መመሪያ ማፅደቁን የግብርና ሚኒስቴር አስታወቀ

ሚኒስቴሩ ችግሩን ለመፍታት በ2016 በጀት ዓመት የሕግ እና ተቋማዊ ማሻሻያዎችን መጀመሩን የገለፀ ሲሆን፣ ይህም የውጭ ኩባንያዎች እና የሀገር ውስጥ የግል ባለሀብቶች በዘር ማባዛትና ስርጭት ስራ ላይ በስፋት እንዲሳተፉ የሚያስችሉ አዳዲስ አዋጆችና መመሪያዎችን ያካተተ ነው።

ይህ አካሄድ ቢሮክራሲን በመቀነስ፣ ምርታማነታቸው ከፍተኛ የሆኑ የዘር ዝርያዎች የእርሻ ወቅትን ሳያስተጓጉሉ በወቅቱ ለአርሶ አደሩ እንዲደርሱ ለማድረግ የታለመ መሆኑን የግብርና ሚኒስቴር ዲኤታ ሶፊያ ካሣ መግለፃቸውን የግል መገናኛ ብዙሃን ዘግበዋል።

​ለዘንድሮ የምርት ዘመን ሚኒስቴሩ 2 ሚሊዮን ኩንታል የተሻሻለ ዘር ለማቅረብ ያቀደ ሲሆን፣ ከዚህ ውስጥ 1.5 ሚሊዮን ኩንታሉ ተጠቃሚ አርሶ አደሮች ዘንድ ይደርሳል ተብሎ ይጠበቃል። በሚኒስቴሩ መረጃ መሠረት፣ እስካሁን 6.8 ሚሊዮን ኩንታል የሚጠጉ የተለያዩ የዘር ዓይነቶች በክልል የአቅርቦት መረቦች በኩል ተሰራጭተዋል።

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X

አዳዲስ ዜናዎች
0