የኒውክሌር ኃይል ልማት የኢትዮጵያን የኢንዱስትሪ ልማት ሽግግር ለማፋጠን አስፈላጊነ ነው - የኢትዮጵያ የኒውክሌር ኃይል ኮሚሽን

© telegram sputnik_ethiopiaየኒውክሌር ኃይል ልማት የኢትዮጵያን የኢንዱስትሪ ልማት ሽግግር ለማፋጠን አስፈላጊነ ነው - የኢትዮጵያ የኒውክሌር ኃይል ኮሚሽን
የኒውክሌር ኃይል ልማት የኢትዮጵያን የኢንዱስትሪ ልማት ሽግግር ለማፋጠን አስፈላጊነ ነው - የኢትዮጵያ የኒውክሌር ኃይል ኮሚሽን - Sputnik አፍሪካ, 1920, 13.07.2026
ሰብስክራይብ

የኒውክሌር ኃይል ልማት የኢትዮጵያን የኢንዱስትሪ ልማት ሽግግር ለማፋጠን አስፈላጊነ ነው - የኢትዮጵያ የኒውክሌር ኃይል ኮሚሽን

ቀጣይነት ያለው የኢኮኖሚን እድገትን ለማረጋገጥ ሰላማዊ የኒውክሌር ኃይል ልማት አስፈላጊ መሆኑን የኮሚሽኑ ምክትል ኮሚሽነር አብዱረዛቅ ዑመር ተናግረዋል፡፡

“የኃይል አቅርቦት ኃይል ማመንጨትን፣ ማስተላለፍን ፣ ማከፋፈልን እና ለተጠቃሚ ማድረስን የሚያካትት ረጅም ሂደት ያለው በመሆኑ  የበርካታ ዓመታት እቅድ እና ጥናት እና ኢንቨስትመንትን ይፈልጋል።” ብለዋል።

በኢትዮጵያ የኃይል ልማት እቅድ ውስጥ ትኩረት ከተሰጣቸው የኃይል አማራጮች ኒውክሌርን ለሰላማዊ አገልግሎት ማልማት እና መጠቀም አንዱ መሆኑን ምክትል ኮሚሽነሩ አመላክተዋል።

ባለሥልጣኑ ይህን መልዕክት ያስተላለፉት የኢትዮጵያ የኒውክሌር ኃይል ኮሚሽን ከዓለም አቀፉ የአቶሚክ ኤነርጂ ኤጀንሲ እና የአፍሪካ የኒውክሌር ጥናት እና ልማት የትብብር ማዕቀፍ ስምምነት ጋር በመተባበር  በኃይል እቅድ ዝግጅት እና የፍላጎት ግምገማ ላይ ያተኮረ ሥስልጠና ማስጀመሪያ ሥነ-ስርዓት ላይ ነው፡፡

ከተለያዩ ዩንቨርሲቲዎች የተውጣጡ መምህራን፣ ተመራማሪዎች እና የዘርፉ ባለሙያዎች የሚሳተፉት ይህ ሥልጠና ዛሬን ጨምሮ ለ12 ቀናት  እንደሚቆይ የስፑትኒክ አፍሪካ ባልደረባ ዘግቧል፡፡

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X

© telegram sputnik_ethiopia
የኒውክሌር ኃይል ልማት የኢትዮጵያን የኢንዱስትሪ ልማት ሽግግር ለማፋጠን አስፈላጊነ ነው - የኢትዮጵያ የኒውክሌር ኃይል ኮሚሽን - Sputnik አፍሪካ
1/2
© telegram sputnik_ethiopia
የኒውክሌር ኃይል ልማት የኢትዮጵያን የኢንዱስትሪ ልማት ሽግግር ለማፋጠን አስፈላጊነ ነው - የኢትዮጵያ የኒውክሌር ኃይል ኮሚሽን - Sputnik አፍሪካ
2/2
1/2
2/2
አዳዲስ ዜናዎች
0