በ2025/26 ሩሲያ ወደ አፍሪካ የላከችው የስንዴ ምርት ከፍተኛ ደረጃ ላይ ደርሷል ተባለ

በ2025/26 ሩሲያ ወደ አፍሪካ የላከችው የስንዴ ምርት ከፍተኛ ደረጃ ላይ ደርሷል ተባለ
የሩሲያ መገናኛ ብዙኃን ‘አግሮኤክስፖርት’ን ጠቅሰው እንደዘገቡት፣ ከሰሃራ በታች ወዳሉ የአፍሪካ ሀገራት የተላከው የስንዴ መጠን በግምት 6.7 ሚሊዮን ቶን ደርሷል። ይህም ከ2024/25 የምርት ዘመን ጋር ሲነጻጸር በ3 በመቶ፣ እንዲሁም ከአምስት ዓመት አማካይ አቅርቦት ጋር ሲነጻጸር በ34 በመቶ ብልጫ አለው።
ከፍተኛ መጠን ያለው የስንዴ አቅርቦት የተረከቡ ሀገራት፦
ግብፅ፦ 10 ሚሊዮን ቶን፣ የ27 በመቶ ጭማሪ፣
ሱዳን፦ በግምት 2.2 ሚሊዮን ቶን፤
ኬንያ፦ በግምት 1.8 ሚሊዮን ቶን፣ ከአምስት ዓመት አማካይ በ83 በመቶ ብልጫ፤
ታንዛኒያ፦ በግምት 0.9 ሚሊዮን ቶን፣ የ49 በመቶ ጭማሪ፤
ዩጋንዳ፦ በግምት 0.5 ሚሊዮን ቶን፣ የ83 በመቶ ጭማሪ፤
ጅቡቲ፦ ከ350 ሺህ ቶን በላይ፣ የ100 በመቶ ጭማሪ፤
ሶማሊያ፦ በግምት 230 ሺህ ቶን፣ የ200 በመቶ ጭማሪ።
የአቅርቦት መዳረሻዎችን ማስፋፋት የፍላጎት መለዋወጥ የሚያስከተለውን ተጽዕኖ እንደሚቀንስ የጠቀሰው አግሮኤክስፖርት፤ ከሰሃራ በታች ያሉ የአፍሪካ ሀገራት እያደገ የመጣው ሚና ሩሲያ በአፍሪካ የምታደርገውን የእህል ወጪ ንግድ ለማስፋፋት በምታከናውነው ተግባር ውስጥ ቁልፍ አካል እንደሚሆን አፅንዖት ሰጥቷል።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X