https://amh.sputniknews.africa/20260713/4631702.html
ሩሲያ እና ቱንዚያ ለአፍሪካ መረጋጋት ትብብራቸውን እንደሚያጠናክሩ ላቭሮቭ ተናገሩ
ሩሲያ እና ቱንዚያ ለአፍሪካ መረጋጋት ትብብራቸውን እንደሚያጠናክሩ ላቭሮቭ ተናገሩ
Sputnik አፍሪካ
ሩሲያ እና ቱንዚያ ለአፍሪካ መረጋጋት ትብብራቸውን እንደሚያጠናክሩ ላቭሮቭ ተናገሩ የሩሲያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር የሁለቱ ሀገራት የዲፕሎማሲ ግንኙነት የተመሰረተበትን 70ኛ ዓመት አስመልክተው ለቱንዚያው አቻቸው መሐመድ አሊ ናፍቲ በላኩት የእንኳን... 13.07.2026, Sputnik አፍሪካ
2026-07-13T10:19+0300
2026-07-13T10:19+0300
2026-07-13T10:24+0300
sputnik africa
telegram sputnik_ethiopia
https://cdn.amh-img.sputnikglobe.com/img/07ea/07/0d/4631549_0:82:1280:802_1920x0_80_0_0_09a9b1295111bc558b8b3b7303582105.jpg
ሩሲያ እና ቱንዚያ ለአፍሪካ መረጋጋት ትብብራቸውን እንደሚያጠናክሩ ላቭሮቭ ተናገሩ የሩሲያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር የሁለቱ ሀገራት የዲፕሎማሲ ግንኙነት የተመሰረተበትን 70ኛ ዓመት አስመልክተው ለቱንዚያው አቻቸው መሐመድ አሊ ናፍቲ በላኩት የእንኳን አደረሳችሁ የቴሌግራም መልዕክት፣ በአካባቢው ደህንነትንና መረጋጋትን በማስፈን ረገድ ያላቸውን የጋራ ፍላጎት አፅንዖት ሰጥተው ገልጸዋል።ላቭሮቭ፣ “የሩሲያ እና የቱንዚያ ግንኙነት ለሁለቱ ሀገራት ህዝቦች ጥቅም፣ እንዲሁም በአፍሪካ እና በሜዲትራኒያን ቀጣና መረጋጋትና ደህንነትን ለማረጋገጥ በሚያስችል መልኩ በተሳካ ሁኔታ መጠናከሩን እንደሚቀጥል ሙሉ እምነት አለኝ” ሲሉ ተናግረዋል።በሞስኮ እና በቱንዚያ መካከል ያለው ትስስር በወዳጅነት እና በጋራ መከባበር ላይ የተገነባ ረጅም ታሪክ ያለው መሆኑን የጠቀሱት ሚኒስትሩ፣ በነዚህ አሥርት ዓመታት ውስጥ ሁለቱ ወገኖች በባለብዙ ዘርፍ የሁለትዮሽ ትብብር ላይ ከፍተኛ ልምድ ማካበታቸውንና ይህም በሂደት እያደገ መምጣቱን አክለዋል።በእንግሊዘኛ ያንብቡ ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X
Sputnik አፍሪካ
feedback.africa@sputniknews.com
+74956456601
MIA "Rossiya Segodnya"
2026
Sputnik አፍሪካ
feedback.africa@sputniknews.com
+74956456601
MIA "Rossiya Segodnya"
ዜናዎች
am_ET
Sputnik አፍሪካ
feedback.africa@sputniknews.com
+74956456601
MIA "Rossiya Segodnya"
https://cdn.amh-img.sputnikglobe.com/img/07ea/07/0d/4631549_52:0:1229:883_1920x0_80_0_0_8698e767ce83c8da2a41f6a22f5857df.jpgSputnik አፍሪካ
feedback.africa@sputniknews.com
+74956456601
MIA "Rossiya Segodnya"
sputnik africa, telegram sputnik_ethiopia
sputnik africa, telegram sputnik_ethiopia
ሩሲያ እና ቱንዚያ ለአፍሪካ መረጋጋት ትብብራቸውን እንደሚያጠናክሩ ላቭሮቭ ተናገሩ
10:19 13.07.2026 (የተሻሻለ: 10:24 13.07.2026) ሩሲያ እና ቱንዚያ ለአፍሪካ መረጋጋት ትብብራቸውን እንደሚያጠናክሩ ላቭሮቭ ተናገሩ
የሩሲያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር የሁለቱ ሀገራት የዲፕሎማሲ ግንኙነት የተመሰረተበትን 70ኛ ዓመት አስመልክተው ለቱንዚያው አቻቸው መሐመድ አሊ ናፍቲ በላኩት የእንኳን አደረሳችሁ የቴሌግራም መልዕክት፣ በአካባቢው ደህንነትንና መረጋጋትን በማስፈን ረገድ ያላቸውን የጋራ ፍላጎት አፅንዖት ሰጥተው ገልጸዋል።
ላቭሮቭ፣ “የሩሲያ እና የቱንዚያ ግንኙነት ለሁለቱ ሀገራት ህዝቦች ጥቅም፣ እንዲሁም በአፍሪካ እና በሜዲትራኒያን ቀጣና መረጋጋትና ደህንነትን ለማረጋገጥ በሚያስችል መልኩ በተሳካ ሁኔታ መጠናከሩን እንደሚቀጥል ሙሉ እምነት አለኝ” ሲሉ ተናግረዋል።
በሞስኮ እና በቱንዚያ መካከል ያለው ትስስር በወዳጅነት እና በጋራ መከባበር ላይ የተገነባ ረጅም ታሪክ ያለው መሆኑን የጠቀሱት ሚኒስትሩ፣ በነዚህ አሥርት ዓመታት ውስጥ ሁለቱ ወገኖች በባለብዙ ዘርፍ የሁለትዮሽ ትብብር ላይ ከፍተኛ ልምድ ማካበታቸውንና ይህም በሂደት እያደገ መምጣቱን አክለዋል።
በእንግሊዘኛ ያንብቡ
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X