የሱዳን ፍርድ ቤት በአማፂው የፈጥኖ ደራሽ ኃይል መሪ እና ሌሎች ከፍተኛ አዛዦች በሌሉበት የሞት ፍርድ ፈረደባቸው

© telegram sputnik_ethiopiaየሱዳን ፍርድ ቤት በአማፂው የፈጥኖ ደራሽ ኃይል መሪ እና ሌሎች ከፍተኛ አዛዦች በሌሉበት የሞት ፍርድ ፈረደባቸው
የሱዳን ፍርድ ቤት በአማፂው የፈጥኖ ደራሽ ኃይል መሪ እና ሌሎች ከፍተኛ አዛዦች በሌሉበት የሞት ፍርድ ፈረደባቸው - Sputnik አፍሪካ, 1920, 13.07.2026
ሰብስክራይብ

የሱዳን ፍርድ ቤት በአማፂው የፈጥኖ ደራሽ ኃይል መሪ እና ሌሎች ከፍተኛ አዛዦች በሌሉበት የሞት ፍርድ ፈረደባቸው

የአማፂው ከፊል ወታደራዊ ቡድን መሪ መሐመድ ሐምዳን ዳጋሎ እና የወንድሙን አብደልራሂም ሐምዳን ዳጋሎን ጨምሮ 15 ሌሎች ግለሰቦች በጦር ወንጀል፣ በሰብአዊነት ላይ በተፈጸሙ ወንጀሎች፣ በዘር ማጥፋት እና በንፁሃኖ ላይ ጥቃት በመፈጸም ጥፋተኛ ሆነው ተገኝተዋል፡፡

ውሳኔው እ.ኤ.አ. በሚያዝያ 2023 ጦርነቱ ከተጀመረ ወዲህ በፈጥኖ ደራሽ ኃይሎች አመራሮች ላይ የተላለፈ የመጀመሪያው የፍርድ ቤት ብይን ነው፡፡

ቁልፍ ዝርዝሮች፦

ክሱ፦ የምዕራብ ዳርፉር ገዥ የነበሩትን ኻሚስ አባከር ሰኔ 2023፣ ፈጥኖ ደራሽ ኃይሉ በንፁሃኖች ላይ ጥቃት እያደረሰ ነው ብለው በከሰሱ በጥቂት ሠዓታት ውስጥ መገደላቸውን በተመለከተ ነው፡፡ በወቅቱ በኤል-ገነይና በተቀሰቀሰው በዚሁ ዓመፅ አብዛኞቹ የማሳሊት ብሔረሰብ አባላት የሆኑ ከ10,000 እስከ 15,000 የሚደርሱ ሰዎች ተገድለዋል።

ቀጣዩ እርምጃ፦ ፍርድ ቤቱ መዝገቡን ለጠቅላይ ፍርድ ቤት የሚመራው ሲሆን፣ ፍርደኞቹ በቁጥጥር ስር ለማዋልና አሳልፎ ለመስጠት በኢንተርፖል በኩል ጥረት ያደርጋል።

በእንግሊዘኛ ያንብቡ

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X

አዳዲስ ዜናዎች
0