ቶጎ የ2026ቱን የኤቫላ ባህላዊ የትግል ፌስቲቫል አስጀመረች
19:05 12.07.2026 (የተሻሻለ: 19:14 12.07.2026)
© telegram sputnik_ethiopia
ሰብስክራይብ
ቶጎ የ2026ቱን የኤቫላ ባህላዊ የትግል ፌስቲቫል አስጀመረች
በየዓመቱ የሚከናወነው የካብዬ የሰዎች የጉልምስና የሽግግር ሥርዓት፣ ወጣቶች ወደ አዋቂነት ምዕራፍ የሚሸጋገሩበትን ጊዜ የሚያመለክት ሲሆን፣ የጀግንነት፣ የዲሲፕሊን፣ የጽናት እና የአንድነት እሴቶችንም የሚያሰርጽ ነው።
የማስጀመሪያው ሥነ-ሥርዓቱ በትናንትናው ዕለት በፒያ የተከናወነ ሲሆን፣ በበርካታ ወረዳዎች የሚካሄዱ የትግል ግጥሚያዎችን እና ባህላዊ ሁነቶችን ያካተተው ይህ በዓል እስከ ሐምሌ 11 ቀን ድረስ ይቆያል።
ይህ ፌስቲቫል ባህላዊ ቅርሶችን ጠብቆ ለማቆየት እና በቀጣናው ያለውን ቱሪዝም ለማነቃቃት ትልቅ እገዛ ያደርጋል ተብሎ እንደሚጠበቅ የሀገሪቱ ፕሬዝዳንት መሥሪያ ቤት ባወጣው መግለጫ አስታውቋል።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X