ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ በኳታር የቀድሞ አሚር ሕልፈተ ሕይወት ሐዘናቸውን ገለፁ፤ የአሚሩን የአሸማጋይነት ሚናም አስታወሰዋል
17:58 12.07.2026 (የተሻሻለ: 18:04 12.07.2026)

© telegram sputnik_ethiopia
ሰብስክራይብ
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ በኳታር የቀድሞ አሚር ሕልፈተ ሕይወት ሐዘናቸውን ገለፁ፤ የአሚሩን የአሸማጋይነት ሚናም አስታወሰዋል
ሼክ ሃማድ ቢን ኸሊፋ አል ታኒ ሰላምን ለማጠናከር እና ለውይይትና ድርድር መሠረት ለመጣል የሚጥሩ ጥበበኛ መሪ ነበሩ ሲሉ ጠቅላይ ሚኒስትሩ በማኅበራዊ የትስስር ገፃቸው ላይ ጽፈዋል።
“የእሳቸው ማለፍ ለአፍሪካም ሆነ ለመላው ቀጣና ትልቅ ኪሳራ ነው” ብለዋል።
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ በሁለቱ አገራት መካከል ያለውን ታሪካዊ ግንኙነት ያነሱ ሲሆን፣ ሼክ ሃማድ እ.አ.አ በሚያዚያ 2013 በኢትዮጵያ ያደረጉትን ይፋዊ የሥራ ጉብኝት ለትብብር አዳዲስ አማራጮችን የከፈተ እና ለስትራቴጂካዊ አጋርነት መሠረት የጣለ ትልቅ ምዕራፍ እንደነበር አስታውሰዋል።
ጠቅላይ ሚኒስትሩ በኢትዮጵያ እና በኳታር መካከል ያለው ጠንካራ ወንድማማችነት በአሁኑ አሚር በሼክ ታሚም ቢን ሃማድ አል ታኒ መሪነት ይበልጥ እየጎለበተ እንደሚቀጥል ያላቸውን እምነት ጨምረው ገልጸዋል።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X