በአዲስ አበባ የኮንስትራክሽን ማዕድናትን ለማውጣት የአካባቢ ተፅዕኖ ግምገማ ማቅረብ ግዴታ የሚያደርግ አዲስ መመሪያ ወጣ
14:50 12.07.2026 (የተሻሻለ: 14:54 12.07.2026)

© telegram sputnik_ethiopia
ሰብስክራይብ
በአዲስ አበባ የኮንስትራክሽን ማዕድናትን ለማውጣት የአካባቢ ተፅዕኖ ግምገማ ማቅረብ ግዴታ የሚያደርግ አዲስ መመሪያ ወጣ
የከተማዋ አካባቢ ጥበቃ ባለሥልጣን እንደ ጥቁር ድንጋይ፣ ጠጠር፣ አሸዋ እና አፈር ያሉ የኮንስትራክሽን ማዕድናት ማውጣት ሥራዎችን በሕጋዊ ማዕቀፍ ለመምራት አዲስ መመሪያ ማውጣቱን የግል መገናኛ ብዙኃን ዘግበዋል።
በመመሪያው መሠረት አዲስ ፈቃድ ፈላጊዎች ማመልከቻቸውን በባለሥልጣኑ የድረ-ገጽ በኩል ሲያቅርቡ፣ ሕጋዊ የመሬት ባለቤትነት ማረጋገጫ፣ የአዋጭነት ጥናት እና የጸደቀ የአካባቢ ተፅዕኖ ግምገማ ሰነድ ማያያዝ ይጠበቅባቸዋል። ይሁን እንጂ ግለሰቦች በራሳቸው ይዞታ ላይ ለንግድ ያልሆነ የኮንስትራክሽን አገልግሎት ብቻ የሚውሉ ማዕድናትን ያለ ፈቃድ ክፍያ ማውጣትና መጠቀም ይችላሉ።
መመሪያው ለአካባቢ ጥበቃ ሲባል ጥብቅ ገደቦችን የጣለ ሲሆን፤ ልዩ ሁኔታዎች ካልገጠሙ በቀር በመቃብሮች፣ በሃይማኖታዊ ስፍራዎች፣ በታሪካዊ ቅርሶች፣ በጥበቃ ስር ባሉ ዞኖች፣ በብሔራዊ ፓርኮች፣ በኢንዱስትሪ ፓርኮች እንዲሁም ከመኖሪያ መንደሮች በ500 ሜትር ርቀት ክልል ውስጥ ፈቃድ እንደማይሰጥ አስታውቋል።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X