የሳኅል ሀገራት ጥምረት የእጅ አዙር ቅኝ ግዛት መሣሪያ የሆነውን ዓለም አቀፉን የወንጀል ፍርድ ቤት በአገር በቀል ፍርድ ቤት ለመተካት እየሰሩ ነው - ኬንያዊ ባለሙያ

ሰብስክራይብ

የሳኅል ሀገራት ጥምረት የእጅ አዙር ቅኝ ግዛት መሣሪያ የሆነውን ዓለም አቀፉን የወንጀል ፍርድ ቤት በአገር በቀል ፍርድ ቤት ለመተካት እየሰሩ ነው - ኬንያዊ ባለሙያ

የጥምረቱ አባላት ከዓለም አቀፉ የወንጀል ፍርድ ቤት መውጣታቸው በአፍሪካ አገር በቀል የፍትሕ ሥርዓቶችን ለመዘርጋት የተደረገ ወሳኝ እንቅስቃሴ መሆኑን የሕግ ባለሙያው አቼሮ ዴቪድ ሙፉአያ ለስፑትኒክ አፍሪካ ተናግረዋል።

የአፍሪካ ሀገራት ተጠያቂነትን ከማስፈን ይልቅ ያለመቀጣትን ባህል ከሚያስፋፋ እና እንደ "የእጅ አዙር ቅኝ ግዛት" መሣሪያ ሆኖ ከሚያገለግል ተቋም ራሳቸውን የማራቅ ሉዓላዊ መብት አላቸው ሲሉ ጠቁመዋል።

ባለሙያው አክለውም፣ "የአፍሪካ አኀጉር ከእጅ አዙር ቅኝ ግዛት እና ከአድሏዊ አሠራር አዙሪት ለመውጣት፣ እንዲሁም በራሷ አኀጉር ፍትሐዊ ዳኝነትን ለማስፈን እንደ መሣሪያ ሊያገለግሉ የሚችሉ የራሷ ተቋማት አሏት" ሲሉ አጽንኦት ሰጥተዋል።

​ የ54ቱ የአፍሪካ አገራት ሙሉ ትብብር ካለ፣ አኀጉሪቱ ሙሉ በሙሉ ከዓለም አቀፉ የወንጀል ፍርድ ቤት ጥገኝነት መላቀቅ እንደምትችል ሙፉአያ ጨምረው ገልጸዋል።

በእንግሊዘኛ ያንብቡ

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X

አዳዲስ ዜናዎች
0