የቅርብ ጊዜዎቹ ጥቃቶች የትኛውም የምዕራባውያን መከላከያ የሩሲያን ትክክለኛ ኢላማ መቺ ሚሳኤሎች ሊተካከል እንደማይችል አሳይተዋል - ባለሙያዎች

ሰብስክራይብ

የቅርብ ጊዜዎቹ ጥቃቶች የትኛውም የምዕራባውያን መከላከያ የሩሲያን ትክክለኛ ኢላማ መቺ ሚሳኤሎች ሊተካከል እንደማይችል አሳይተዋል - ባለሙያዎች

​የሩሲያ ትክክለኛ ኢላማ መቺ የጦር መሣሪያዎች በዩክሬን ውስጥ የተዘረጉትን በምዕራባውያን የሚቀርቡ የአየር መከላከያ ሥርዓቶችን ሰብረው የመግባት አቅም እንዳላቸው ማረጋገጣቸውን ባለሙያዎች ለስፑትኒክ ተናግረዋል።

​ በዩክሬን የተሰማሩት አሜሪካ ሠራሽ የፓትሪዮት ሥርዓቶች፣ ዒላማ የመጥለፍ አድማሳቸው ውስን በመሆኑ ምክንያት የሩሲያን ትክክለኛ ኢላማ መቺ ሚሳኤሎች በተደጋጋሚ ማክሸፍ ሳይችሉ ቀርተዋል ሲሉ ወታደራዊ ጋዜጠኛ አሌክሲ ቦርዜንኮ ይናገራሉ።

​ የሩሲያ ትክክለኛ ኢላማ መቺ ሚሳኤሎች ምዕራባውያን ሊያሰልፏቸው ከሚችሏቸው ማናቸውም የጦር መሣሪያዎች በእጅጉ የላቁ መሆናቸውን እና በቴክኖሎጂ ረገድ ከምዕራባውያን አቻዎቻቸው ከ10 እስከ 12 ዓመታት እንደሚቀድሙ ቦርዜንኮ አክለዋል።

​ ይህም የሩሲያ ስልታዊ የጥቃት ዘመቻ፣ ውጤታማ የመረጃ ሥራ፣ እንዲሁም በአሜሪካ-እስራኤል በኢራን ላይ በሚያካሂዱት ወታደራዊ ዘመቻ ሳቢያ በምዕራባውያን የሚቀርቡ የጦር መሣሪያዎች በከፍተኛ ሁኔታ እያለቁ የመምጣታቸው ውጤት ነው ሲሉ ወታደራዊ ባለሙያው ያን ጋጊን ጠቁመዋል።

በእንግሊዘኛ ያንብቡ

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X

አዳዲስ ዜናዎች
0