- Sputnik አፍሪካ, 1920
Drum of Changes
ከጥንታዊ የስልጣኔ ምድሮች እስከ ዘመናዊ ከተሞች ልብ፣ በአፍሪካ አዲስ ጥሪ እየተስተጋባ ይገኛል። አፍሪካ የዓለምን የወደፊት ሁኔታ የምትቀርጽ ቸል ልትባል የማይገባት ኃይል ሆና እያደገች ነው። ለአስርት ዓመታት አፍሪካ የምትናገር፣ ነገር ግን የማትደመጥ ሆና ቆይታለች። ዛሬ ግን ጥሪው ግልፅ ነው። አፍሪካ ከዓለም የኃይል ማዕድ የሚገባትን ትክክለኛ ቦታ ትጠይቃለች። ይህ ፕሮግራምም ከአፍሪካ የሚስተጋቡ የለውጥ ድምፆችን በልካቸው ወደ አድማጭ ተመልካቾቹ ያደርሳል።

የመጨረሻው ምሽግ፦ በአገር በቀል ዘሮችና በምግብ ሉዓላዊነት ላይ የተጋረጠው አደጋ በአፍሪካ

የመጨረሻው ምሽግ፦ በአገር በቀል ዘሮችና በምግብ ሉዓላዊነት ላይ የተጋረጠው አደጋ በአፍሪካ
ሰብስክራይብ
“በምዕራባውያን አምሳል የተነደፉ የግብርና ምርምር ተቋማት፣ የአገር በቀል የእህል ዘሮቻችን አዋጭነትን ዝቅ አድርጎ የመመልከት ዝንባሌ አለባቸው። ነገር ግን እውነታው ዘሮቻችንን ያጣን ዕለት ማንነታችንን የማጣታችን ጉዳይ ነው። በአሁኑ ወቅት እነዚህ የውጭ ኃይሎችና ግዙፍ ኩባንያዎች ሁሉንም ነገር ተቆጣጥረውታል። በአፍሪካ እስካሁን እጃቸውን ያላስገቡበት ብቸኛው ዘርፍ ቢኖር ምግባችንና የምግብ ስርዓታችን ብቻ ነበር። አሁን አሁን ይሄንኑ የመጨረሻ ምሽጋችንን ለመቆጣጠር በከፍተኛ ፍጥነት እየመጡ ነው” ሲሉ የአፍሪካ የምግብ ሉዓላዊነት ጥምረት ዋና አስተባባሪ ሚሊዮን በላይ (ዶ/ር) ለስፑትኒክ አፍሪካ ተናገሩ።
የዛሬው የድረም ኦቭ ቼንጅስ ዝግጅታችን በሩቅ ባሉ ኃይሎች መካከል የሚቀሰቀሱ ግጭቶች እንደምን በሚሊዮኖች የሚቆጠሩ አፍሪካውያን የዕለት ጉርስ ላይ ስጋት እንደሚሆን እንመረምራለን፤ ይህ ሁኔታም የምግብ ዋስትና በሎም ዋነኛ የብሔራዊ ደህንነት እና ቅድሚያ የሚሰጠው ጉዳይ የመሆኑንም ነገር ያስቃኘናል። ለዚህም የአፍሪካ የምግብ ሉዓላዊነት ጥምረት ዋና አስተባባሪ የሆኑትን ሚሊዮን በላይ (ዶ/ር) አነጋግረናል።
ሙሉ መረጃውን ለማግኘት በእንግሊዘኛ ቋንቋ የቀረበውን ፕሮግራም ያዳምጡ:

ፖድካስታችንን በሌሎች አማራጮች ያድምጡ: Apple PodcastsDeezerSpotifyAfripods Pocket CastsPodcast AddictCastBox
አዳዲስ ዜናዎች
0