የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የስፖርት ማዘውተሪያ ስፍራዎችን ለማስተዳደር የሚያስችል የኦንላይን ሥርዓት ይፋ አደረገ
15:54 11.07.2026 (የተሻሻለ: 16:04 11.07.2026)

© telegram sputnik_ethiopia
ሰብስክራይብ
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የስፖርት ማዘውተሪያ ስፍራዎችን ለማስተዳደር የሚያስችል የኦንላይን ሥርዓት ይፋ አደረገ
አዲሱ አሰራር ቀደም ሲል ይነሱ የነበሩ የፍትሐዊ አጠቃቀም ቅሬታዎችን እና የአሰራር ውስብስብነቶችን በዘላቂነት ለመፍታት ያቀደ ሲሆን፣ በሁለት ክፍለ ከተሞች በሙከራ ፕሮጀክትነት ተተግብሮ ውጤታማ በመሆኑ ወደ ሁሉም ክፍለ ከተሞች እና ወረዳዎች እንዲተላለፍ መደረጉን የከተማ አስተዳደሩ ወጣቶችና ስፖርት ቢሮ አስታውቋል።
1,730 የስፖርት ማዘውተሪያዎች ወደ መረጃ ቋት (ዳታቤዝ) የገቡ ሲሆን 59 የእግር ኳስ ሜዳዎች በአሁኑ ወቅት አገልግሎት እየሰጡ ይገኛሉ። ቀሪዎቹ ማዘውተሪያዎችም በጥቂት ቀናት ውስጥ ሙሉ ለሙሉ ወደ ሥርዓቱ እንደሚገቡ ቢሮው ገልጿል።
ታዳጊዎች፣ አካል ጉዳተኞች እና መክፈል የማይችሉ የሕብረተሰብ ክፍሎች ከዚህ የኦንላይን ክፍያ ነጻ ሆነው ቀደም ሲል በየአካባቢው በተዘጋጀላቸው ፕሮግራም መሰረት አገልግሎቱን እንደሚያገኙ ይፋ ተደርጓል።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X