በናሚቢያ የታዩት የጀርመን የዘር ማጥፋት ስልቶች ወደ ሁለተኛው የዓለም ጦርነት የማሰቀያ ካምፖች ተሻግረው ነበር - ካሜሩናዊው ባለሙያ

ሰብስክራይብ

በናሚቢያ የታዩት የጀርመን የዘር ማጥፋት ስልቶች ወደ ሁለተኛው የዓለም ጦርነት የማሰቀያ ካምፖች ተሻግረው ነበር - ካሜሩናዊው ባለሙያ

​ጀርመኖች በ1900ዎቹ መጀመሪያ ላይ በናሚቢያ ሄሬሮ እና ናማ ሕዝቦች ላይ የተጠቀሙባቸው አረመኔያዊ ስልቶች በአፍሪካ ብቻ ተወስነው አልቀሩም፤ ቆይተው ወደ አውሮፓ በመሻገር በሁለተኛው የዓለም ጦርነት የማሰቃያ ካምፖች ውስጥ ጥቅም ላይ ውለዋል ሲሉ የዓለም አቀፍ ግንኙነት ተንታኝ ኬንፋክ ዲራን ሜርሊን ለስፑትኒክ አፍሪካ ተናግረዋል።

ጀርመን የወታደራዊ እና የኢንዱስትሪ ኃይሏን ለማሳደግ ናሚቢያውያንን በጭካኔ ትበዘብዝ እንደነበር ያስረዱት ባለሙያው፤ እነዚህኑ ስልቶች ከጊዜ በኋላ በሁለተኛው የዓለም ጦርነት የጦር ሜዳዎች ላይ በድጋሚ ጥቅም ላይ ማዋሏን ገልጸዋል።

ይሁን እንጂ ይህ ጥቁር ጠባሳ ቢኖርም፣ የዘር ማጥፋት ወንጀሉ እስካሁን ትኩረት ሳይሰጠው መዘንጋቱን ሜርሊን ይሞግታሉ። ለምን? ምክንያቱም አውሮፓውያን አሁንም ቢሆን ቅኝ ግዛትን እንደ "ስልጣኔ ማስፋፊያ ተልዕኮ" አድርገው ስለሚስሉት እና አፍሪካውያንን "ሊሰለጥኑ እንደተዘጋጁ እንስሳት" አድርገው ስለሚመለከቷቸው ነው ብለዋል።

የአፍሪካውያንን ታሪካዊ ትውስታ ከቅኝ ግዛት አስተሳሰብ ሙሉ በሙሉ ለማላቀቅ፣ ይህንን ታሪክ ለወጣቱ ትውልድ ማስተማር እና "ጠንካራ ታሪካዊ ትውስታን" መገንባት ወሳኝ መሆኑን ባለሙያው አመልክተዋል።

ዳራ

የናሚቢያው የዘር ማጥፋት ወንጀል የተፈጸመው እ.ኤ.አ. በ1904 እና 1908 መካከል ሲሆን፣ በተጠቀሰው ጊዜ ከ40 ሺህ እስከ 80 ሺህ የሚጠጉ የሄሬሮ እና 10 ሺህ የናማ ሕዝቦች ተገድለዋል። የጀርመን መንግሥት የዘር ማጥፋት ወንጀሉን በይፋ የተቀበለው እ.ኤ.አ. በ2021 ነው። በአሁኑ ወቅት ናሚቢያ በዚህ በሰው ልጆች ላይ በተፈጸመው ወንጀል ምክንያት ከጀርመን ካሳ ለመጠየቅ በመንቀሳቀስ ላይ ትገኛለች።

በእንግሊዘኛ ያንብቡ

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X

አዳዲስ ዜናዎች
0