ናይጄሪያውያን ሙስሊሞች ለኢራኑ መንፈሳዊ መሪ ምልክታዊ የቀብር ሥነ-ሥርዓት አካሄዱ
20:10 10.07.2026 (የተሻሻለ: 20:34 10.07.2026)
© telegram sputnik_ethiopia
ሰብስክራይብ
ናይጄሪያውያን ሙስሊሞች ለኢራኑ መንፈሳዊ መሪ ምልክታዊ የቀብር ሥነ-ሥርዓት አካሄዱ
ለአያቶላ ኻሜኒ ክብር ለመስጠት በመላው ናይጄሪያ ምልክታዊ የቀብር ሥነ-ሥርዓቶች መካሄዳቸውን መገናኛ ብዙኃን ዘግበዋል።
በካዱና ግዛት ሐዘንተኞች በሶባ አካባቢ ምሳሌያዊ የሬሳ ሣጥን በመያዝ አስከሬን የመሸኘት ሥነ-ሥርዓት አካሂደዋል።
በሌላ በኩል በሰሜን ምዕራብ በሚገኘው የካኖ ግዛት፤ ልክ በቴህራን እንደተካሄደው ይፋዊ የስንብት ሥነ-ሥርዓት አጋርነታቸውን ለማሳየት እና የተሰማቸውን ጥልቅ ሐዘን ለመግለጽ የድጋፍ ሰልፍ ማድረጋቸው ተገልጿል።
አያቶላ ኻሜኒ እና የቤተሰባቸው አባላት በትናንትናው ዕለት በኢራኗ መሽሃድ ከተማ ተቀብረዋል።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X
© telegram sputnik_ethiopia