ኬንያ ቀጣናዊ የንግድ ትስስርን ለማሳደግ የስታንዳርድ ጌጅ ባቡር መስመሯን ከኢትዮጵያ ጋር ለማገናኘት ማቀዷ ይፋ ተደረገ

© telegram sputnik_ethiopiaኬንያ ቀጣናዊ የንግድ ትስስርን ለማሳደግ የስታንዳርድ ጌጅ ባቡር መስመሯን ከኢትዮጵያ ጋር ለማገናኘት ማቀዷ ይፋ ተደረገ
ኬንያ ቀጣናዊ የንግድ ትስስርን ለማሳደግ የስታንዳርድ ጌጅ ባቡር መስመሯን ከኢትዮጵያ ጋር ለማገናኘት ማቀዷ ይፋ ተደረገ - Sputnik አፍሪካ, 1920, 10.07.2026
ሰብስክራይብ

ኬንያ ቀጣናዊ የንግድ ትስስርን ለማሳደግ የስታንዳርድ ጌጅ ባቡር መስመሯን ከኢትዮጵያ ጋር ለማገናኘት ማቀዷ ይፋ ተደረገ

 

ዕቅዱ የላሙ ወደብ-ደቡብ ሱዳን-ኢትዮጵያ የትራንስፖርት ኮሪደር (ላፕሴት) አካል ነው።

 

የባቡር መስመሩ ከ50 እስከ 60 ሚሊዮን ሕዝብ ካለው ገበያ ጋር እንደሚያገናኝና በሂደት ወደ ደቡብ ሱዳን የማሻገር ውጥን እንዳለ የኬንያ የትራንስፖርት ሚኒስቴር ዋና ጸሐፊ መሐመድ ዳጋር አስታውቀዋል።

 

የባቡር መስመር ማራዘሚያው ከኢትዮጵያ ጋር ያለውን ንግድ የሚያሻሽል እና ቀጣናዊ ትስስር የሚደግፍ ነው መባሉን የኬንያ ሚዲያ ዘግቧል። ከላሙ እስከ ኢትዮጵያ ለሚዘልቀው የመስመር ክፍል የተለየ የጊዜ ሰሌዳ ወይም የወጪ ዝርዝር መረጃ አልተጠቀሰም።

 

🪣 የላፕሴት ኮሪደር 2,900 ኪሎ ሜትር የስታንዳርድ ጌጅ ባቡር መስመር ዝርጋታን፣ የድፍድፍ ዘይትና የተጣራ ነዳጅ ማስተላለፊያ ቧንቧዎችን እንዲሁም አውራ ጎዳናዎችን ያካትታል።

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X

አዳዲስ ዜናዎች
0