ኢትዮጵያ በ2026 ሁለተኛ ሩብ ዓመት ዝቅተኛ የኤሌክትሪክ ክፍያ ከሚያስከፍሉ አምስት የአፍሪካ ሀገራት በቀዳሚነት ተቀመጠች
18:15 10.07.2026 (የተሻሻለ: 18:24 10.07.2026)

© telegram sputnik_ethiopia
ሰብስክራይብ
ኢትዮጵያ በ2026 ሁለተኛ ሩብ ዓመት ዝቅተኛ የኤሌክትሪክ ክፍያ ከሚያስከፍሉ አምስት የአፍሪካ ሀገራት በቀዳሚነት ተቀመጠች
በዓለም አቀፍ ደረጃ አማካኝ የቤት ውስጥ የኤሌክትሪክ ኃይል ዋጋ በኪሎዋት ሰዓት 0.176 ዶላር ሲሆን አውሮፓውያን ከፍተኛውን 0.254 ዶላር ሲከፍሉ፤ እስያ ደግሞ ዝቅተኛውን ቀጣናዊ አማካኝ 0.088 ዶላር አስመዝግባለች። በርካታ የአፍሪካ ሀገራት ግን ለቤት ውስጥም ሆነ ለንግድ ተጠቃሚዎች እጅግ በጣም ርካሽ ኃይል ያቀርባሉ።
"ግሎባል ፔትሮል ፕራይሰስ" ባወጣው መረጃ መሠረት በጣም ተመጣጣኝ የኤሌክትሪክ ክፍያ ተመን ያላቸው አምስት የአፍሪካ ሀገራት የሚከተሉት ናቸው
1⃣ ኢትዮጵያ፦ ለቤት አገልግሎት በኪሎ ዋት ሰዓት 0.006 ዶላር፤ ለንግድ በኪሎ ዋት ሰዓት 0.018 ዶላር።
2⃣ አንጎላ፦ ለቤት አገልግሎት በኪሎ ዋት ሰዓት 0.016 ዶላር፤ ለንግድ በኪሎ ዋት ሰዓት 0.013 ዶላር።
3⃣ ግብፅ፦ ለቤት አገልግሎት በኪሎ ዋት ሰዓት 0.023 ዶላር፤ ለንግድ በኪሎ ዋት ሰዓት 0.038 ዶላር።
4⃣ ዛምቢያ፦ ለቤት አገልግሎት በኪሎ ዋት ሰዓት 0.023 ዶላር፤ ለንግድ በኪሎ ዋት ሰዓት 0.040 ዶላር።
5⃣ ናይጄሪያ፦ ለቤት አገልግሎት በኪሎ ዋት ሰዓት 0.036 ዶላር፤ ለንግድ በኪሎ ዋት ሰዓት 0.050 ዶላር።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X