የኢትዮጵያ የክትባት ማምረቻ ፋብሪካ ዲዛይን ሥራ እየተጠናቀቀ እንደሆነ ተገለፀ
18:22 09.07.2026 (የተሻሻለ: 18:24 09.07.2026)

© telegram sputnik_ethiopia
ሰብስክራይብ
የኢትዮጵያ የክትባት ማምረቻ ፋብሪካ ዲዛይን ሥራ እየተጠናቀቀ እንደሆነ ተገለፀ
ፋብሪካው የክትባት አቅርቦትን የማሳደግ እና የሕክምና ነጻነትን የማረጋገጥ ዓላማ አለው፡፡
ግንባታው በኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ሆልዲንግ ስር እንደሚከናወን የኢትዮጵያ ምግብና መድኃኒት ባለሥልጣን ዋና ዳይሬክተር ሄራን ገርባ ተናግረዋል።
ከፋብሪካው በተጨማሪ በአዲስ አበባ ቃሊቲ አካባቢ የክትባት ምርመራ ማከናወኛ ላቦራቶሪ እየተገነባ መሆኑንም ገልፀዋል።
ይህ ውጥን እ.ኤ.አ በ2040 አፍሪካ 60% የክትባት ፍላጎቷን በራሷ እንድትሸፍን የተቀመጠውን የአፍሪካ ኅብረት ግብ መሠረት ያደረገ ነው መባሉን የሀገር ውስጥ ሚዲያ ዘግቧል።
በሰው ሠራሽ አስተውህሎት የበለጸገ ምሥል
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X