ሮሳቶም በግብጹ የኤል ዳባ የኒውክሌር ኃይል ጣቢያ የሁለተኛውን የኃይል ማመንጫ ክፍል ተከላ ጀመረ
17:55 09.07.2026 (የተሻሻለ: 18:04 09.07.2026)
© telegram sputnik_ethiopia
ሰብስክራይብ
ሮሳቶም በግብጹ የኤል ዳባ የኒውክሌር ኃይል ጣቢያ የሁለተኛውን የኃይል ማመንጫ ክፍል ተከላ ጀመረ
በሥነ-ሥርዓቱ የግብጽ ጠቅላይ ሚኒስትር ሞስጠፋ ማድቡሊ፣ የሮሳቶም ዋና ዳይሬክተር አሌክሲ ሊካቾቭ እና የዓለም አቀፉ የአቶሚክ ኃይል ኤጀንሲ ኃላፊ ራፋኤል ግሮሲ መገኘታቸውን የስፑትኒክ ባልደረባ ዘግቧል።
🟡 ስለ ፕሮጀክቱ፦
የገንዘብ ምንጭ (ፋይናንስ)፦ ጣቢያው የሚገነባው በ25 ቢሊዮን ዶላር የሩሲያ ብድር ድጋፍ ነው።
ሪአክተሮች፦ ጣቢያው እያንዳንዳቸው 1,200 ሜጋ ዋት የማመንጨት አቅም ያላቸው አራት የሦስተኛ ትውልድ ቪቪኢአር-1200 ሪአክተሮች ይኖሩታል።
የሮሳቶም ኃላፊነቶች፦
የጣቢያው ግንባታ፣
የኒውክሌር ነዳጅ አቅርቦት፣
የሀገር ውስጥ ባለሙያዎችን ማሠልጠን፣
ጣቢያው ሥራ ከጀመረ በኋላ ለመጀመሪያዎቹ 10 ዓመታት የማንቀሳቀስ እና የጥገና ሥራዎችን ማከናወን።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X