ሮሳቶም ለግብጹ የኤል ዳባ የኒውክሌር ጣቢያ አራተኛውን የሪአክተር አካል ማምረት ጀመረ

ሰብስክራይብ

ሮሳቶም ለግብጹ የኤል ዳባ የኒውክሌር ጣቢያ አራተኛውን የሪአክተር አካል ማምረት ጀመረ

ለአራተኛው ቪቪኢአር-1200 ሪአክተር የሚሆኑ እያንዳንዳቸው ከ65 ቶን በላይ የሚመዝኑ የመጀመሪያዎቹ የብረት ጥሬ ዕቃዎች ደርሰዋል። እነዚህ ግዙፍ አካላት በተቀመጠው ትክክለኛ መስፈርት መሠረት የሚቀረጹ ሲሆን ለብዙ አሥርት ዓመታት እንዲያገለግሉ ዝገትን በሚከላከል ሽፋን ይሸፈናሉ።

ሮሳቶም ለአንደኛው እና ለሁለተኛው ክፍሎች የሚሆኑ የሪአክተር አካላትን ከዚህ ቀደም ያስረከበ ሲሆን በአሁኑ ወቅት የሚከተሉት መሳሪዎች በምርት ሂደት ላይ ይገኛሉ፦

የክፍል 3 የሪአክተር አካል፣

ከክፍል 2 እስከ 4 ለሚሆኑት ክፍሎች የሚያገለግሉ 12 የእንፋሎት ማመንጫዎች ፣

ሌሎች ቁልፍ የኒውክሌር ማዕከል መሣሪያዎች።

የማምረት ሥራው በሴንት ፒተርስበርግ፣ በሞስኮ፣ በሮስቶቭ እና በካሬሊያ በሚገኙ በተለያዩ የሩሲያ ከተሞች ውስጥ በሚንቀሳቀሱ የሮሳቶም ፋብሪካዎች ውስጥ እየተከናወነ ይገኛል።

በእንግሊዘኛ ያንብቡ

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X

© telegram sputnik_ethiopia
ሮሳቶም ለግብጹ የኤል ዳባ የኒውክሌር ጣቢያ አራተኛውን የሪአክተር አካል ማምረት ጀመረ - Sputnik አፍሪካ
1/3
© telegram sputnik_ethiopia
ሮሳቶም ለግብጹ የኤል ዳባ የኒውክሌር ጣቢያ አራተኛውን የሪአክተር አካል ማምረት ጀመረ - Sputnik አፍሪካ
2/3
© telegram sputnik_ethiopia
ሮሳቶም ለግብጹ የኤል ዳባ የኒውክሌር ጣቢያ አራተኛውን የሪአክተር አካል ማምረት ጀመረ - Sputnik አፍሪካ
3/3
1/3
2/3
3/3
አዳዲስ ዜናዎች
0