ባለፉት 5 ዓመታት ከ25 ሚሊዮን በላይ ለሚሆኑ ዜጎች የንፁህ መጠጥ ውሃ ተደራሽ ሆኗል - የውሃና ኢነርጂ ሚኒስቴር
18:29 08.07.2026 (የተሻሻለ: 18:34 08.07.2026)
© telegram sputnik_ethiopia
ሰብስክራይብ
ባለፉት 5 ዓመታት ከ25 ሚሊዮን በላይ ለሚሆኑ ዜጎች የንፁህ መጠጥ ውሃ ተደራሽ ሆኗል - የውሃና ኢነርጂ ሚኒስቴር
በሀገር አቀፍ ደረጃ ባለፉት አምስት ዓመታት 40 ሺህ አዳዲስ የንፁህ መጠጥ ውሃ ፕሮጀክቶች ተገንብተው ለአገልግሎት መብቃታቸውንም የውሃና ኢነርጂ ሚኒስቴር አስታውቋል።
ይህ ይፋ የተደረገው ለ1.6 ሚሊዮን ሕዝብ አገልግሎት የሚሰጠውና የአዳማ ከተማን የውሃ ፍላጎት ለሚቀጥሉት 10 ዓመታት የሚያረጋግጠው የሞጆ-አዳማ የንፁህ መጠጥ ውሃ ፕሮጀክት በተመረቀበት ወቅት ነው።
15 ጥልቅ የውሃ ጉድጓዶችን እና የ250 ኪሎ ሜትር መስመር ዝርጋታን ያካተተው ይህ ፕሮጀክት፤ በቀን 77 ሺህ ሜትር ኪዩብ ንጹህ ውሃ የማቅረብ አቅም አለው ተብሏል።
በተጠናቀቀው በጀት ዓመት ብቻ 2 ሺህ 233 የውኃ ፕሮጀክቶች ተጠናቀው ለአገልግሎት በመብቃታቸው በኦሮሚያ ክልል 2.5 ሚሊዮን ሕዝብ የንፁህ መጠጥ ውሃ ተጠቃሚ መሆኑን ሚኒስቴሩ አመላክቷል።
ሚኒስቴሩ በቀጣዮቹ 4 ዓመታት 100% የንፁህ መጠጥ ውሃ ተደራሽነትን ለማሳካት ያስችላል ያለውን አዲስ የአስተዳደር ሞዴል በቅርቡ ይፋ ማድረጉ ይታወሳል፡፡
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X