እስራኤል 90 በመቶ የሚሆኑ ዩኒቨርሲቲዎችን በማውደም ቀጣዩን የፍልስጤማውያን ትውልድ እያሰናከለች ነው - አክቲቪስት

ሰብስክራይብ

እስራኤል 90 በመቶ የሚሆኑ ዩኒቨርሲቲዎችን በማውደም ቀጣዩን የፍልስጤማውያን ትውልድ እያሰናከለች ነው - አክቲቪስት

በፕሪቶሪያ ዩኒቨርሲቲ ከፍልስጤም ጋር የአብሮነት ዘመቻ ሊቀመንበር አይሻ ኢሶፕ፤ “በእርግጥም የተቀናጀ የጉልበት ሥርዓት” ነው ሲሉ ለስፑትኒክ አፍሪካ በሰጡት አስተያየት ገልፀዋል።

አክቲቪስቷ ያነሷቸው ዋና ዋና ነጥቦች፦

የፍልስጤም ማኅበረሰብ እስከ ቅርብ ጊዜ ድረስ 98 በመቶ በሚጠጋ የመሠረታዊ ትምህርት ምጣኔ “በተለያዩ የሙያ ዘርፎች ድንቅ ሐኪሞችን፣ ገጣሚያንን፣ ጸሐፊዎችንና ምሁራንን ማፍራት” ችሎ ነበር።

ይሁን እንጂ አሁን ላይ የትምህርት ሥርዓቱን ሙሉ በሙሉ ለማፍረስ እንዲሁም የፍልስጤማውያንን ታሪክ፣ ያለፈ ጊዜ እና የጋራ ትውስታ ለማጥፋት ታስቦ “ላቦራቶሪዎች፣ የታሪክ መዛግብት ፣ ቤተ-መጻሕፍት እና የባሕል ማዕከላት ወድመዋል።”

“ዩኒቨርሲቲዎቹ ሆን ተብሎ እና ታቅዶ ኢላማ መደረጋቸው በጣም ግልጽ ነው” ሲሉ ኢሶፕ አፅንዖት ሰጥተዋል።

የፍልስጤም መምህራን እና ተማሪዎች እነዚህን አጥፊ ኃይሎች በጽናት እንዴት እየተቋቋሙ እንደሆነ ለመረዳት ቪዲዮውን ይመልከቱ።

በእንግሊዘኛ ያንብቡ

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X

አዳዲስ ዜናዎች
0