ኢትዮጵያ ለፍትሐዊ የሰው ሠራሽ አስተውህሎት መሠረተ ልማት ተደራሽነት ጥሪ አቀረበች
ኢትዮጵያ ለፍትሐዊ የሰው ሠራሽ አስተውህሎት መሠረተ ልማት ተደራሽነት ጥሪ አቀረበች
በጄኔቫ በተካሄደው የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የሰው ሠራሽ አስተውህሎት አስተዳደር ዓለም አቀፍ ውይይት ላይ፤ ታዳጊ ሀገራት በዘርፉ እኩል ተወዳዳሪና ተጠቃሚ እንዲሆኑ ፍትሐዊ የመሠረተ ልማት፣ የሀብት እና የዕውቀት ተደራሽነት ሊኖር እንደሚገባ አሳስባለች።
በጄኔቫ የኢትዮጵያ ምክትል ቋሚ መልዕክተኛ አምባሳደር ኃይለሥላሴ ሱባ በፓናል ውይይቱ ላይ ያነሷቸው ዋና ዋና ነጥቦች፦
▪ የሰው ሠራሽ አስተውህሎት ልዩነትን ማጥበብ፦ ታዳጊ ሀገራት በዓለም አቀፉ የኤአይ አስተዳደር ላይ ትርጉም ያለው ተሳትፎ እንዲኖራቸው የቴክኖሎጂ ትብብርን ማጠናከር እና ፍትሐዊ የመሠረተ ልማት፣ የባለሙያ እንዲሁም የኢኖቬሽን ዕድሎች አቅርቦትን ማረጋገጥ የግድ ይላል።
▪ የሀገር ውስጥ አቅም ግንባታ፦ በኢትዮጵያ በዘርፉ የረጅም ጊዜ የምርምርና የፈጠራ አቅምን ለማሳደግ “የመደመር አርቴፊሻል ኢንተለጀንስ ዩኒቨርሲቲ” መቋቋሙን እንዲሁም የ “5 ሚሊዮን ኢትዮጵያውያን ኮደሮች” መርኃ-ግብር ከተቀመጠለት ግብ በላይ 5.05 ሚሊዮን ሰልጣኞችን ቀድሞ መመዝገብ መቻሉን ጠቅሰዋል።
▪ አኅጉራዊ መሪነት፦ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ በአፍሪካ ኅብረት የኤአይ እና የዲጂታል ጤና አምባሳደር ተደርገው መመረጣቸው፤ ኢትዮጵያ በአህጉሪቱ ኃላፊነት የተሞላበት የዲጂታል ሽግግርን ለመምራት እያደረገች ያለውን መሪነት ያሳያል።
ኢትዮጵያ ማንም ወደኋላ የማይቀርበት እና ሰብዓዊ መብትን ማዕከል ያደረገ የዓለም አቀፍ የሰው ሠራሽ አስተውህሎት አስተዳደር ሥርዓት ለመዘርጋት ከተመድ፣ ከአፍሪካ ኅብረት እና ከሌሎች አጋሮች ጋር በቅርበት ለመሥራት ያላትን ዝግጁነት በድጋሚ አረጋግጣለች።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X