ኢራን የአሜሪካን ጥቃት በማውገዝ፤ ሊያስከትል የሚችለውን መዘዝ አስጠነቀቀች
የኢራን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር፤ አሜሪካ በኢራን ደቡባዊ የባሕር ዳርቻ የክትትል ጣቢያዎች ላይ ሌሊቱን የሰነዘረችውን ጥቃት ባወገዘበት መግለጫ፤ ድርጊቱ "የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ቻርተር እና የተኩስ አቁም ስምምነት ሰነዱን በግልጽ የጣሰ ነው" ሲል ኮንኗል።
ከመግለጫው የተወሰዱ ዋና ዋና ነጥቦች፦
▪ የአሜሪካ ጥቃት ሁሉም ወታደራዊ ዘመቻዎች እንዲቆሙ የሚደነግገውን የመግባቢያ ሰነድ አንቀጽ 1 የጣሰ ነው፣
▪ አሜሪካ በስምምነቱ አንቀጽ 10 ሥር የተገባውን ቃል በመጣስ የኢራንን የነዳጅ ሽያጭ ፈቃድ ሰርዛለች፣
▪ እስራኤል በሊባኖስ ላይ የምትፈጽመው ቀጣይነት ያለው ጥቃት ስምምነቱን ይበልጥ ዋጋ ቢስ ያደርገዋል፣
▪ አሜሪካ የዚህ ውጥረት መባባስ ለሚያስከትለው አደገኛ መዘዝ ሙሉ ኃላፊነቱን ትወስዳለች፣
▪ ኢራን ግዛታቸውን ወይም የአየር ክልላቸውን ለአጥቂዎች በማመቻቸት የወንጀል ተባባሪነት ለሚሆኑ የቀጣናው ሀገራት ማስጠንቀቂያ ትሰጣለች፣
▪ የኢራን ጦር ኃይሎች በተመድ ቻርተር አንቀጽ 51 መሠረት ለጥቃቱ ፈጻሚ አካል ቁርጠኛ ምላሽ በመስጠት የሀገሪቱን ሉዓላዊነት ያስጠብቃሉ።
በእንግሊዘኛ ያንብቡ
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X