የላቭሮቭ ጉብኝት የሁለቱን ሀገራት የኢኮኖሚ እና ዲፕሎማሲ ግንኙነት የሚያሳድግ ነው - ኢትዮጵያዊ ባለሙያ
09:34 08.07.2026 (የተሻሻለ: 09:44 08.07.2026)

© telegram sputnik_ethiopia
ሰብስክራይብ
የላቭሮቭ ጉብኝት የሁለቱን ሀገራት የኢኮኖሚ እና ዲፕሎማሲ ግንኙነት የሚያሳድግ ነው - ኢትዮጵያዊ ባለሙያ
የሩሲያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሰርጌ ላቭሮቭ የአዲስ አበባ ጉብኝት፤ ኢትዮጵያ እና ሩሲያ በኒውክሌር ኃይል ማመንጫ ጣቢያ ግንባታ፣ በሳይንስ እና ቴክኖሎጂ እንዲሁም በወታደራዊ ጉዳዮች የሚያጀደርጉትን ትብብር እንደሚያጠናክር፤ የፖሊሲ ጥናት ባለሙያው ሙክረም ሚፍታህ (ዶ\ር) ለስፑትኒክ አፍሪካ ገልጸዋል።
ሩሲያ አዲስ የዓለም ሥርዓት ለመቅረፅ እየተጫወተች ለምትገኘው የመሪነት ሚና ኢትዮጵያ የጎላ አስተዋጽኦ ማድረግ እንደምትችልም ነው ባለሙያው ያከሉት።
"በሚቀጥሉት ዓመታት ትኩረት አድርገው ከሚሠሩባቸው ወሳኝ ዘርፎች አንዱ አዲስ የዓለም ሥርዓት እንዴት መልሶ መቅረጽ እንደሚቻል እንዲሁም ለምሳሌ ሩሲያ፣ ቻይና፣ ኢራን፣ ቱርክ እና እንደ ኢትዮጵያ ያሉ ሀገራት በወደፊቱ ዓለም አቀፍ መድረክ ላይ ሊጫወቱ የሚችሉትን ሚና ይመለከታል።"
በአፍሪካ ኅብረት መቀመጫነቷ የአኅጉሪቱ የፖለቲካ ኃይል የስበት ማዕከል የሆነችው ኢትዮጵያ፤ ሩሲያ የአፍሪካ ሀገራትን ድጋፍ እንድታገኝ በማድረግ ረገድ ቁልፍ ተዋናይ አንደሆነች ሙክረም ሚፍታህ ጨምረው ገልጸዋል።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X