- Sputnik አፍሪካ, 1920
The Rising South
የዓለም አቀፍ የኃይል ሚዛን እየተቀየረ ባለበት በዚህ ወቅት - ኢትዮጵያን፣ አፍሪካን እና ሌሎችን የሚቀርጹ የፖለቲካ፣ የኢኮኖሚ እና የማህበራዊ ሃይሎች ወደምንመለከትበት ወደ “ራይዚንግ ሳዉዝ” እንኳን በደህና መጡ፡፡ ደቡባዊ አመለካከቶችን ወደ ዓለም አቀፋዊ ውይይት መድረክ ስናቀርብ የአሰላሳዮችን ፣ የመሪዎችን እና የለዉጥ ፈጣሪዎችን ሃሳብ ያድምጡ።

ከረግረጋማ መሬት ኢኮኖሚ እስከ ቡና ወጪ ንግድ ስኬት

ከረግረጋማ መሬት ኢኮኖሚ እስከ ቡና ወጪ ንግድ ስኬት
ሰብስክራይብ
"የመንግስት ፖሊሲ በግብርናው ዘርፍ በጎን ከመስፋፋት ይልቅ የተጠናከረ (ምርታማ) ግብርናን መጠቀም አለብን የሚል ነው። የዚህ ግብርና በጎን መስፋፋት ተፅዕኖ ረግረጋማ መሬቶቻችንን በከፍተኛ ሁኔታ እና ከመጠን በላይ እንዲራቆቱ ያደርጋል። ስለዚህ ይህንን በመረዳት ግብርናን ከዘመናዊ ቴክኖሎጂዎች እና ከአግሮፎሬስትሪ ስርዓቶች ጋር በማቀናጀት ችግሩን መቆጣጠር ይኖርብናል።" ሲሉ በወራቤ ዩኒቨርሲቲ የኢኮኖሚክስ መምህርና የዌትላንድስ ኢንተርናሽናል ቀጣናዊ አስተባባሪ መሐመድ ኢሳ (ዶ/ር)ለስፑትኒክ አፍሪካ ተናግረዋል።
በዚህ የራይዚንግ ሳውዝ ዝግጅት ሶስት ቁልፍ ጉዳዮችን እንመለከታለን፡፡ክፍል አንድ፦ የኢትዮጵያ ረግረጋማ መሬቶች (Wetlands) ያላቸው ያልተነካ ኢኮኖሚያዊ እሴት ምንድን ነው በሚለው ዙሪያ በጉዳዩ ላይ የዘርፉ ባለሙያ የሆኑት መሐመድ ኢሳ (ዶ/ር) ሰፊ ማብራሪያ ይሰጡናል። ክፍል ሁለት፦ ኢትዮጵያ በያዝነው 2018 ዓ.ም በጀት ዓመት በቡና ወጪ ንግድ ታሪካዊ የሆነውን 3 ቢሊዮን ዶላር ገቢ እንድታስመዘግብ ያደረጉት ዋና ዋና ስራዎች ምንድን ናቸው? የሚለውን የኢትዮጵያ ቡናና ሻይ ባለሥልጣን ዋና ዳይሬክተር አዱኛ ደበላ (ዶ/ር)ጋር እንዳስሳለን። በመጨረሻው ክፍል በአፍሪካ የሕክምና ትምህርት ሥርዓትን ከውጭ ተጽዕኖ ነጻ በማውጣት ሂድት ከአህጉሪቱ ነባራዊ እውነታዎች ጋር ማጣጣም ለምን አስፈለገ? በሚለው ርዕሰ ጉዳይ የኢትዮጵያ ጤና ፌደሬሽን ም/ፕ ዶ/ር ግርማ አባቢ ጋር ያደረግነውን ቆይታ እናቀርባለን።
ሙሉ መረጃዉን ለማግኘት በእንግሊዝኛ ቋንቋ የቀረበውን ፕሮግራም ያዳምጡ:

ፖድካስታችንን በሌሎች አማራጮች ያድምጡ : Apple PodcastsSpotifyDeezerAfripodsPodcast AddictPocket CastsCastBox
አዳዲስ ዜናዎች
0