የስፑትኒክ ፕሮ የተግባር ልምምድ ፕሮግራም ለአፍሪካውያን ጋዜጠኞች ተጀመረ
20:07 07.07.2026 (የተሻሻለ: 16:50 08.07.2026)

© ስፑትኒክ. አሪና አንቶኖቫ
ሰብስክራይብ
በዓለም አቀፉ የዜና ወኪል እና የሬዲዮ ጣቢያ ስፑትኒክ ዋና መሥሪያ ቤት፣ ከሰሃራ በታች ባሉ የአፍሪካ አገራት ለሚገኙ ወጣት ጋዜጠኞች የተዘጋጀው ልዩ የስፑትኒክ ፕሮ ሥልጠና ተጀምሯል። ፕሮግራሙ የአሌክሳንደር ጎርቻኮቭ የሕዝብ ዲፕሎማሲ ፈንድ እና የሮሶትሩድኒቼስቶቮ “ኒው ጄኔሬሽን” ፕሮጀክት በጋራ ያዘጋጁት የ“ኢንተሩሲያ” የልምምድ ሥልጠና አካል ነው።
ይህየበጋወቅትሥልጠና የአፍሪካን አህጉር ከሚወክሉ መሪ የሚዲያ ተቋማትና ድርጅቶች የተውጣጡ 10 ተወካዮችን ያካተተ ሲሆን፤ እነሱም፦ የካሜሩን የመገናኛ ሚኒስቴር፣ ኦብዘርቨር ሚዲያ ሊሚትድ (ዩጋንዳ)፣ ኤቢፒ የዜና ወኪል (ብሩንዲ)፣ ዜድኤንቢሲ ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬሽን (ዛምቢያ)፣ ሶና ብሔራዊ የዜና ወኪል (ሶማሊያ)፣ ኤፒኤስ የዜና ወኪል (ሴኔጋል)፣ ኪጋሊ ቱዴይ ሊሚትድ (ሩዋንዳ)፣ ሚዲያፎርዴቨሎፕመንት (ሞዛምቢክ)፣ ኢንዲፔንደንት ሚዲያ (ደቡብ አፍሪካ) እና ዘ ስታር ፐብሊኬሽንስ ሊሚትድ (ኬንያ) ናቸው።

የስፑትኒክ ፕሮ የተግባር ልምምድ ፕሮግራም ለአፍሪካውያን ጋዜጠኞች ተጀመረ
© ስፑትኒክ. አሪና አንቶኖቫ
ይህፕሮግራም ለውጭ አገር ጋዜጠኞች ከሩሲያ የሚዲያ አጀንዳዎች ጋር ለመተዋወቅ፣ ከስፑትኒክ መሪ ባለሙያዎች ለመማር እና ከተለያዩ አገራት ከመጡ የሥራ ባልደረቦቻቸው ጋር ልምድ ለመለዋወጥ ዕድል ይሰጣል። ለአንድ ወር በሚቆየው በዚህ ቆይታቸው ተሳታፊዎቹ በሥልጠናዎች፣ በተግባራዊ ወርክሾፖች እና በጋራ አጋር ኩነቶች ላይ ይታደማሉ።
በመጀመሪያው ቀን ተሳታፊዎቹ ስለዚህ ጥንቁቅ እና ሰፊ ሙያዊ ፕሮግራም ያላቸውን አመለካከትና የሚጠብቁትን ውጤት አካፍለዋል።

የስፑትኒክ ፕሮ የተግባር ልምምድ ፕሮግራም ለአፍሪካውያን ጋዜጠኞች ተጀመረ
© ስፑትኒክ. አሪና አንቶኖቫ
የኬንያው “ዘ ስታር” ጋዜጠኛ ሲንዲ ካረን አሉኦች እንዲህ ብላለች፦
“ለእኔ ይህ በጣም ስሜታዊ ያደረገኝ፣ ትልቅ ክብር የተሰማኝ እና እጅግ ደስ ያለኝ አጋጣሚ ነው። ስለዚህ ይህ ለእኔ እውን የሆነ ህልም እና በጣም እፈልገው የነበረ ነገር ነው። በእርግጥም አግኝቼዋለሁ። [...] እኔ የምኖረው፣የምተነፍሰው፣ የማየው፣ የምናገረው እና የምመገበው ሚዲያን በመሆኑ፤ ስፑትኒክ እንዴት እንደሚሠራ እና እዚህ ያለው የሚዲያ ተቋም እንዴት እንደሚንቀሳቀስ ለማየትና ብዙ ነገር ለመማር ተስፋ አደርጋለሁ። በመሆኑም እዚህ በመገኘቴ በጣም ደስተኛ ነኝ።”

የስፑትኒክ ፕሮ የተግባር ልምምድ ፕሮግራም ለአፍሪካውያን ጋዜጠኞች ተጀመረ
© ስፑትኒክ. አሪና አንቶኖቫ
የሶማሊያውሶና (SONNA) ብሔራዊ የዜና ወኪል ዋና አዘጋጅ ካድር አዌይስ ሀሰን፣ ጥንቁቅ የሆኑ የሥልጠና ክፍለ-ጊዜዎችን እና ከሚዲያ ባልደረቦቹ ጋር ውጤታማ የሆነ ግንኙነት እንዲኖር ይጠብቃል። በተጨማሪም ስፑትኒክ እና ሶና የረጅም ጊዜ እና የጋራ ተጠቃሚነትን የሚያረጋግጥ ትብብር እንደሚመሠርቱ ያለውን ተስፋ ገልጿል።

የስፑትኒክ ፕሮ የተግባር ልምምድ ፕሮግራም ለአፍሪካውያን ጋዜጠኞች ተጀመረ
© ስፑትኒክ. አሪና አንቶኖቫ
የሴኔጋል የዜና ወኪል ጋዜጠኛ የሆነችው ካዲዲያቱ ሜንዲ በበኩሏ የሚከተለውን አስተያየት ሰጥታለች፦
“በሩሲያ እና በአፍሪካ መካከል ስላለው ትብብር፣ በተለይም በጋዜጠኝነት እና በኮሙኒኬሽን ረገድ ያለውን አመለካከት ለመለዋወጥ ችለናል። [...] ሁላችንምከዚህፕሮግራም እንደምንጠብቀው ሁሉ—የበለጸገ ልምድ እና ሰፊ የሥራ ዕቅድ (አጀንዳ) እናገኛለን፤ ምክንያቱም እዚህ እርስ በርሳችን እንተዋወቃለን፣ እንዲሁም ከሩሲያ ከመጡ ተጨማሪ ጋዜጠኛ ባልደረቦች ጋር እንገናኛለን። ትልቁ ትርፍ ይሄ ነው። እናም በእርግጥ፣ ሥራችንን ለማሻሻል፣ በዚህ ፕሮግራም ያገኘነውን ዕውቀት ሁሉ በየማኅበረሰባችን ውስጥ ለማካተት እና የተሻለ የጋዜጠኝነት ሥራ ለመለማመድ የምንወስደውን ልምድ ሁሉ ይዘን ወደ አገራችን እንመለሳለን።”

የስፑትኒክ ፕሮ የተግባር ልምምድ ፕሮግራም ለአፍሪካውያን ጋዜጠኞች ተጀመረ
© ፎቶ ሮሶትሩድኒቼስቶቮ