ናይጄሪያ በሜታ*፣ ጉግል እና ኤክስ ኩባንያዎች ላይ የውድድር ቁጥጥር ምርመራ ጀመረች
20:05 07.07.2026 (የተሻሻለ: 20:14 07.07.2026)

© telegram sputnik_ethiopia
ሰብስክራይብ
ናይጄሪያ በሜታ*፣ ጉግል እና ኤክስ ኩባንያዎች ላይ የውድድር ቁጥጥር ምርመራ ጀመረች
የናይጄሪያ ፕሬዚዳንት ቦላ ቲኑቡ የሀገሪቱ የውድድር ተቆጣጣሪ አካል በትልልቅ የቴክኖሎጂ ኩባንያዎች ላይ የውድድር ሕግን በሚጥሱ አሠራሮች እና የዜና ይዘቶችን ያለፈቃድ በመጠቀም ዙሪያ ምርመራ እንዲያደርግ መመሪያ መስጠታቸውን የፌዴራል የውድድር እና የሸማቾች ጥበቃ ኮሚሽን ሰኞ ዕለት አስታውቋል።
ኮሚሽኑ ምርመራ እንደሚያደርግባቸው የገለጻቸው ዋና ዋና ጉዳዮች፦
▪ ኩባንያዎቹ በገበያ ላይ ያላቸውን ያልተገደበ የበላይነት፣
▪ ነፃ ውድድርን የሚያደናቅፉ ድርጊቶች፣
▪ የቅጂ መብት ያላቸውን የዜና ይዘቶች ያለፈቃድ ለንግድ ሥራ ማዋል፣
▪ የጋዜጠኝነት ሥራዎችንና ግብዓቶችን 'የሰው ሠራሽ አስተውህሎት ማመንጫ' ሞዴሎችን ለማሠልጠን መጠቀም።
ሜታ* በአክራሪ ድርጊቶች በሩሲያ የታገደ ተቋም ነው።
በሰው ሠራሽ አስተውህሎት የመነጨ ምሥል
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X