በኢትዮጵያ የሞባይል ተጠቃሚዎች 97 ሚሊዮን፣ የኢንተርኔት ደግሞ 61 ሚሊዮን ደረሰ

ሰብስክራይብ

በኢትዮጵያ የሞባይል ተጠቃሚዎች 97 ሚሊዮን፣ የኢንተርኔት ደግሞ 61 ሚሊዮን ደረሰ

የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር ያለፈው በጀት ዓመት የሥራ አፈጻጸሙን አስመልክቶ ባወጣው ሪፖርት፤ በሀገሪቱ የዲጂታል ትራንስፎርሜሽን፣ የቴክኖሎጂ ልማት እና የሥራ ዕድል ፈጠራ ላይ መሻሻሎች መመዝገባቸውን አስታውቋል።

የበጀት ዓመቱ ተጨማሪ ቁልፍ አፈፃፀሞች፦

የብሔራዊ መታወቂያ ተመዝጋቢዎች ቁጥር 48 ሚሊዮን ደርሷል።

በምርምር፣ በፈጠራ እና በስታርትአፕ ተነሳሽነቶች 183 አዳዲስ ቴክኖሎጂዎች እንዲለሙና ድጋፍ እንዲያገኙ ተደርጓል።

በቴክኖሎጂ ሽግግር እና በፈጠራ ሥራዎች አማካኝነት 18,173 አዳዲስ የሥራ ዕድሎች ተፈጥረዋል።

420 የንግድ ተቋማት የኤሌክትሮኒክስ ንግድን የተቀላቀሉ ሲሆን፤ በ'መሶብ' የተቀናጀ አገልግሎት አማካኝነት የሚሰጡ ኦንላይን የመንግሥት አገልግሎቶች ሽፋን 32 በመቶ ደርሷል።

ሚኒስቴሩ የተመዘገቡት ስኬቶች መልካም የሚባሉ ቢሆንም፤ በቀጣዩ በጀት ዓመት የሀገሪቱን የፈጠራ ሥነ-ምህዳር ይበልጥ ለማጠናከር የላቀ ጥረት እና የተሻለ ቅንጅት እንደሚያስፈልግ አፅንዖት ሰጥቷል።

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X

አዳዲስ ዜናዎች
0