በአዲስ አበባ 9.4 ቢሊዮን ብር ግምት ያለው የክረምት በጎ ፈቃድ አገልግሎት መርኃ-ግብር ተጀመረ

© telegram sputnik_ethiopiaበአዲስ አበባ 9
በአዲስ አበባ 9 - Sputnik አፍሪካ, 1920, 07.07.2026
ሰብስክራይብ

በአዲስ አበባ 9.4 ቢሊዮን ብር ግምት ያለው የክረምት በጎ ፈቃድ አገልግሎት መርኃ-ግብር ተጀመረ

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከ3 ሚሊዮን በላይ ነዋሪዎችን ተጠቃሚ የሚያደርግ፣ ከ2 ሚሊዮን በላይ በጎ ፈቃደኞችን የሚያሳትፍ እና እስከ ጥቅምት 2019 ዓ.ም የሚቆይ የክረምት በጎ ፈቃድ አገልግሎት መርኃ-ግብር በይፋ አስጀምሯል።

🟠በከተማዋ የኅብረተሰብ ተሳትፎና በጎ ፈቃድ ማስተባበሪያ ኮሚሽን አማካኝነት “በጎ ፈቃደኝነት ለአዲስ አበባ ዕድገት” በሚል መሪ ቃል የተጀመረው ይህ ዘመቻ፦

▪ ነፃ ሕክምና፦ ለ110 ሺህ አነስተኛ ገቢ ላላቸው ነዋሪዎች ነፃ የሕክምና አገልግሎት መስጠት፣

▪ ደም ልገሳ፦ 25 ሺህ ዩኒት ደም ለመሰብሰብ የሚያስችል ንቅናቄ ማደራጀት፣

▪ ማኅበራዊ ድጋፎች፦ ማዕድ ማጋራት፣ የአረጋውያን እና አቅመ ደካሞች የመኖሪያ ቤት ግንባታ፣ የችግኝ ተከላ እና የክረምት ማጠናከሪያ ትምህርት መስጠትን ያካትታል።

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X

አዳዲስ ዜናዎች
0