ጅማ ዩኒቨርሲቲ በሽታን የሚቋቋሙና ከፍተኛ ምርት የሚሰጡ 1 ሚሊዮን የቡና ችግኞችን እያሰራጨ መሆኑን ገለፀ
17:15 07.07.2026 (የተሻሻለ: 17:24 07.07.2026)
© telegram sputnik_ethiopia
ሰብስክራይብ
ጅማ ዩኒቨርሲቲ በሽታን የሚቋቋሙና ከፍተኛ ምርት የሚሰጡ 1 ሚሊዮን የቡና ችግኞችን እያሰራጨ መሆኑን ገለፀ
የቡና ዝርያዎቹ በዩኒቨርሲቲው የግብርና እና እንስሳት ሕክምና ኮሌጅ የምርምር ተቋም አማካኝነት በሦስት ካምፓሶች የበለፀጉ ሲሆን ለዚሁ ተግባር የሚውል 120 ቶን የተፈጥሮ ማዳበሪያ መዘጋጀቱም ተመላክቷል።
የቡና ችግኞቹ በአጭር ጊዜ ውስጥ ከፍተኛ ምርት መስጠት የሚችሉ በመሆናቸው፤ የአርሶ አደሩንና የባለሀብቶችን ምርታማነት እንዲሁም የኑሮ ደረጃ የሚሻሻሉ ናቸው መባሉን የሀገር ውስጥ ሚዲያ ዘግቧል።
ለዘንድሮው የክረምት የአረንጓዴ ዐሻራ መርኃ-ግብር ከተዘጋጁት 1 ሚሊዮን የተሻሻሉ የቡና ችግኞች በተጨማሪ ከ500 ሺህ በላይ የፍራፍሬ፣ የውበት እና የሀገር በቀል ዕፅዋት ችግኞችን ለመትከል መታቀዱን ዩኒቨርስቲው ገልጿል።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X