በኢቦላ ቫይረስ ክትባቶች ላይ የሚደረጉ ምርምሮችን ለማፋጠን ዝግጁ ስለመሆኗ ሩሲያ ገለጸች

© telegram sputnik_ethiopiaበኢቦላ ቫይረስ ክትባቶች ላይ የሚደረጉ ምርምሮችን ለማፋጠን ዝግጁ ስለመሆኗ ሩሲያ ገለጸች
በኢቦላ ቫይረስ ክትባቶች ላይ የሚደረጉ ምርምሮችን ለማፋጠን ዝግጁ ስለመሆኗ ሩሲያ ገለጸች - Sputnik አፍሪካ, 1920, 07.07.2026
ሰብስክራይብ

በኢቦላ ቫይረስ ክትባቶች ላይ የሚደረጉ ምርምሮችን ለማፋጠን ዝግጁ ስለመሆኗ ሩሲያ ገለጸች

በተለያዩ የአፍሪካ ሀገራት ጉብኝት ለማድረግ አዲስ አበባ የገቡት የሩሲያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሰርጌ ላቭሮቭ፤ ከአፍሪካ ኅብረት ኮሚሽን ሊቀመንበር መሐሙድ ዓሊ ዩሱፍ ጋር አኅጉራዊ ጤናን የተመለከቱ መረጃዎች ተለዋውጠዋል።

በቅርቡ ከተከሰተው የኢቦላ ቫይረስ ወረርሽኝ ጋር በተያያዘ ሩሲያ ጥረቶችን ለማገዝ ዝግጁ ነኝ ስለማለቷ መሐሙድ ዓሊ ዩሱፍ ገልጸዋል።

ሩሲያ ከአሁን ቀደምም ቫይረሱን ለመመርመርና ዝርያዎቹን ለይቶ ለማጥናትና ለመተንተን የሚያስችሉ መሳሪያዎች ድጋፍ ማድረጓን ያስታወሱም ሲሆን የቫይረሱን ዝርያዎች ካገኘሁ ለእነሱ የሚሆን የክትባት ምርምር ሂደት ለማፋጠን ዝግጁ ነኝ ማለቷን የኮሚሽኑ ሊቀመንበር አድንቀዋል።

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X

አዳዲስ ዜናዎች
0