ኢትዮጵያ እና ብራዚል በቱሪዝም ልማት እና ኢንቨስትመንት ዘርፍ በትብብር ለመሥራት ተስማሙ
15:46 07.07.2026 (የተሻሻለ: 15:54 07.07.2026)

© telegram sputnik_ethiopia
ሰብስክራይብ
ኢትዮጵያ እና ብራዚል በቱሪዝም ልማት እና ኢንቨስትመንት ዘርፍ በትብብር ለመሥራት ተስማሙ
ኢትዮጵያ እና ብራዚል በቱሪዝም ልማት ላይ ያለቸውን የሁለትዮሽ ትብብር ለማጠናከር እና ዘላቂ የቱሪዝም ሥራዎችን በጋራ ለማስፋፋት የሚያስችል የመግባቢያ ስምምነት ተፈራርመዋል።
ስምምነቱን በብራዚል የኢትዮጵያ አምባሳደር ልዑልሰገድ ታደሰ እና የብራዚል የቱሪዝም ሚኒስትር ጉስታቮ ኮስታ ፌሊሲያኖ ፈርመውታል።
የስምምነቱ ዋና ዋና ነጥቦች፦
የሁለቱን ሀገራት የቱሪዝም መዳረሻዎች በጋራ ማስተዋወቅ፣ የቱሪስቶችን ፍሰት ማሳደግ እና አዳዲስ የቱሪዝም ኢንቨስትመንት ዕድሎችን መፍጠር፣
የመረጃ እና የባለሙያ ልውውጥ ማድረግ፣ ተቋማዊ ትብብርን ማጠናከር እንዲሁም የአቅም ግንባታ እና የሥልጠና ተነሳሽነቶችን ማስፋፋት።
አምባሳደር ልዑልሰገድ ስምምነቱ በሁለትዮሽ መስመሮች ብቻ ሳይሆን በብሪክስ እና በሌሎች ባለብዙ ወገን መድረኮች ያለውን ትብብር ይበልጥ እንደሚያጠናክር ገልጸዋል።
የብራዚሉ የቱሪዝም ሚኒስትር ጉስታቮ ኮስታ በበኩላቸው፤ ብራዚል ከኢትዮጵያ ጋር በዘርፉ ያላትን ግንኙነት ለማስፋፋት እና አዳዲስ የኢንቨስትመንት ዕድሎችን በጋራ ለመፈተሽ ቁርጠኛ መሆኗን አረጋግጠዋል።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X