የስልጢ-ቡታጅራ ጂኦፓርክ በዩኔስኮ ለመመዝገብ የሚያስፈልጉ መስፈርቶች ሙሉ በሙሉ ተሟልተዋል - ቱሪዝም ሚኒስቴር
19:45 06.07.2026 (የተሻሻለ: 19:54 06.07.2026)

© telegram sputnik_ethiopia
ሰብስክራይብ
የስልጢ-ቡታጅራ ጂኦፓርክ በዩኔስኮ ለመመዝገብ የሚያስፈልጉ መስፈርቶች ሙሉ በሙሉ ተሟልተዋል - ቱሪዝም ሚኒስቴር
የቱሪዝም ሚኒስቴር እና የዩኔስኮ አዲስ አበባ ቢሮ ልዑካን ቡድን በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል እያካሄደ ያለውን የመስክ ምልከታና ማረጋገጫ ተከትሎ፤ የስልጢ እና ቡታጅራ ጂኦፓርክ በዩኔስኮ መዝገብ ውስጥ ለመስፈር የሚያስችሉ መመዘኛዎችን በሙሉ ማሟላቱ ተገልጿል።
የተከናወኑ ተግባራት፦
ባለፉት ሁለት ዓመታት በታዋቂ የኢትዮጵያ ጂኦሎጂስቶች የተጠኑ ዓለም አቀፍ ጥናቶች ታትመዋል፡፡
የዩኔስኮ አስፈላጊ ሰነዶችን የማዘጋጀት ሥራ ሙሉ በሙሉ ተጠናቋል።
የባህል፣ ታሪክና ተፈጥሮ ውሕደት ማረጋገጫ እንዲሁም በስምጥ ሸለቆ አካባቢ ያሉ የጥናት መረጃዎች ተደራጅተዋል።
የቱሪስቶች መረጃ ሰጪ ማዕከላት፣ አቅጣጫ ጠቋሚ ምልክቶች፣ ቢልቦርዶችና የመረጃ ፓናሎች ተዘጋጅተዋል።
ፓርኩ የምዝገባ ሂደቱን አልፎ ዕውቅን የሚያገኝ ከሆነ በዩኔስኮ የተመዘገበ የሀገሪቱ የመጀመሪያው ጂኦፓርክ መሆን ይችላል።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X

1/3
© telegram sputnik_ethiopia

2/3
© telegram sputnik_ethiopia

3/3
© telegram sputnik_ethiopia
1/3
© telegram sputnik_ethiopia
2/3
© telegram sputnik_ethiopia
3/3
© telegram sputnik_ethiopia