የአፍሪካ የጤና ችግሮች በአኅጉሪቱ ተጨባጭ ሁኔታዎች ላይ የተመሠረቱ አፍሪካዊ መፍትሄዎችን ይሻሉ - ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ
19:19 06.07.2026 (የተሻሻለ: 19:24 06.07.2026)

© telegram sputnik_ethiopia
ሰብስክራይብ
የአፍሪካ የጤና ችግሮች በአኅጉሪቱ ተጨባጭ ሁኔታዎች ላይ የተመሠረቱ አፍሪካዊ መፍትሄዎችን ይሻሉ - ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ
ባልተመጣጠነ ከፍተኛ የበሽታዎች ጫና ውስጥ የምትገኘው አፍሪካ በነባራዊ እውነታዎቿ ላይ የተመሠረተ አፍሪካዊ መፍትሔ እንደሚያስፈልጋት ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ በ2ኛው የአፍሪካ የሕክምና ትምህርት ጉባኤ መድረክ ላይ ባደረጉት ንግግር አሳስበዋል።
ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ በንግግራቸው በአኅጉሪቱ የጤና ዘርፍ ላይ ጫና እያሳደሩ ያሉ ተግዳሮቶችን ለይተዋል፡፡ እነሱም፦
የጤና ባለሙያዎችና አሠልጣኞች እጥረት፣
የሥልጠና መሠረተ-ልማት አለመሟላት፣
የሠለጠኑ ሠራተኞች ስደት (ፍልሰት)፣
ወረርሽኝ፣ የአየር ንብረት ለውጥ፣ ስደት እና ምጣኔ ሀብታዊ ጉዳዮች ናቸው፡፡
በመሆኑም አፍሪካ ለጤና ችግሮቿ የሚሆንና ተጨባጭ እውነታዎቿን ከግምት ያስገባ አፍሪካዊ መፍትሔ እንደሚያስፈልጋትም አጽንኦት መስጠታቸውን የስፑትኒክ አፍሪካ ባልደረባ ዘግቧል።
የጤናው ዘርፍ በትናንት እሳቤዎች ሊመራ እንደማይችል የገለጹት ተመስገን ጥሩነህ፣ ዘመኑን በዋጁ የቴክኖሎጂና የፈጠራ ውጤቶች ሊታገዝና በሥርዓተ ትምህርት ሊያካትት እንደሚገባም ጠቁመዋል፡፡
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X