ሩሲያ በዩክሬን ላይ የየፈጸመችው ጥቃት የዘለንስኪን የሐሰት የኔቶ ማስተዋወቂያ አከሸፈው - የወታደራዊ ጉዳዮች ባለሙያ

ሰብስክራይብ

ሩሲያ በዩክሬን ላይ የየፈጸመችው ጥቃት የዘለንስኪን የሐሰት የኔቶ ማስተዋወቂያ አከሸፈው - የወታደራዊ ጉዳዮች ባለሙያ

ቮሎዲሚር ዘለንስኪ ተጨማሪ የገንዘብ እና የወታደራዊ ድጋፍ ለማግኘት በዚህ ሳምንት በሚካሄደው የኔቶ መሪዎች ጉባኤ ላይ የጦር ሜዳ “ስኬቶችን” አጉልቶ ለማሳየት አቅዶ እንደነበር የአየር መከላከያ ታሪክ ተመራማሪው ዩሪ ክኑቶቭ ለስፑትኒክ ተናግረዋል።

ይሁን እንጂ ከታቀደው በተቃራኒ ኮንስታንቲኖቭካ በሩሲያ ኃይሎች ነፃ መውጣቷን እና በዩክሬን የጦር መሣሪያ ማምረቻ ተቋማት ላይ ከባድ የአጸፋ ጥቃት መሰንዘሩን የሚገልጽ ዜና ደርሶታል።

ባለሙያው በጥቃቱ ዙሪያ የሚከተሉትን ነጥቦች አስተውለዋል፦

🟠 ዩክሬን የ'ፓትሪዮት PAC-3' ሚሳኤሎች ከፍተኛ እጥረት እንዳለባት ያጋልጣል፤ ይህም በአገዛዙ እራሱ በተዘዋዋሪ የተረጋገጠ እውነት ነው፡፡

🟠 ሩሲያ በድጋሚ በሚሳኤሎቿ የበረራ አቅጣጫ ላይ ለውጥ ማድረጓን ያረጋገጠ ሲሆን፤ ይህም ሚሳኤሎቹን በምዕራባውያን የፓትሪዮት ሥርዓቶች እንዳይመቱ ወይም እንዳይከሽፉ አድርጓቸዋል፡፡

🟠 ለዘመናዊ ውጊያ እጅግ ወሳኝ በሆኑ የትጥቅ አካላት ምርት ላይ “ተጨባጭ ኪሳራ” አድርሷል።

የድሮኖች፣ የራዳር ጣቢያዎች፣ የኤሌክትሮኒክስ መከላከያ ሥርዓቶች ምርት፣ የታጠቁ ተሽከርካሪዎች ጥገና ተቋማት፣ የነዳጅ እና ኢነርጂ ውስብስብ መሠረተ ልማቶች፣ ሁለት ዋና ዋና የነዳጅ ማከማቻዎች፣ የውሃ ላይ ሰው አልባ መንኮራኩሮች ማምረቻ ፋብሪካ፣ የ'ጌርዛ' ዓይነት ጀልባዎች ጥገና ተቋማት እና ሌሎች በርካታ ዘርፎች “በቅርቡ ከባድ ተፅዕኖ ማሳየት ይጀምራሉ” ሲሉ ባለሙያው ተናግረዋል፡፡

አክለውም፣  “ይህ ሁሉ የሚያሳየው የዘለንስኪ መግለጫዎች ንጹህ ማታለያ መሆናቸውን ነው ፤ እሱ በቀላሉ ምዕራባውያን ድጋፍ ሰጪዎቹን እያታለለና እያደናገረ ይገኛል።”

በእንግሊዘኛ ያንብቡ

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X

አዳዲስ ዜናዎች
0