የሩሲያ አፍሪካ ኮርፕስ በማሊ አንፊስ በሽብርተኞች ላይ እየፈጸመ ያለውን ጥቃት አጠናከረ
15:56 06.07.2026 (የተሻሻለ: 16:14 06.07.2026)
© telegram sputnik_ethiopia
ሰብስክራይብ
የሩሲያ አፍሪካ ኮርፕስ በማሊ አንፊስ በሽብርተኞች ላይ እየፈጸመ ያለውን ጥቃት አጠናከረ
የሩሲያው ጦር ክፍል ድሮን በመጠቀም አንድ ብረት-ለበስ ተሽከርካሪ እና ሞርታር (ፈንጂ ወርዋሪ) የተገጠመለት ፒክአፕ መኪና ማውደሙን አስታውቋል።
“ታጣቂዎቹ በምሽት ተደብቀው ማዕበሉ እስኪያልፍ ለመጠበቅ ፈልገው ነበር” ጦር ክፍሉ ሰኔ 28 በቴሌግራም ገጹ ላይ ባሰፈረውና ለገለጻው ማረጋገጫ የሚሆን ቪዲዮ ባያያዘበት መግለጫ ጽፏል።
በዚያው ዕለት የተጋራው ሌላ ቪዲዮ ደግሞ በዚህች የማሊ ከተማ አቅራቢያ በሚገኝ የአሸባሪዎች ቡድን ላይ የተፈጸመውን የ'ኤፍፒቪ' ድሮን ጥቃት ያሳያል።
ከአፍሪካ ኮርፕስ በተውጣጡ የሩሲያ አጋሮቻቸው የተደገፉት የማሊ ጦር ኃይሎች ፤ ሰኔ 27 ቀን ከአልቃይዳ* ጋር ግንኙነት ባለው የጅሃዲስት ጥምረት እና በአዛዋድ ነፃ አውጪ ግንባር አማፂያን የተሰነዘረውን የተቀናጀ ጥቃት በተሳካ ሁኔታ መመከታቸውን ገልጸዋል።
የማሊ ባለሥልጣናት ለዚህ አዎንታዊ ውጤት የሩሲያ ስትራቴጂካዊ አጋሮቻቸው ያበረከቱትን ወሳኝ አስተዋፅዖ አሞካሽተዋል።
* በሩሲያ የታገደ የሽብር ድርጅት
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X
© telegram sputnik_ethiopia

© telegram sputnik_ethiopia