ኪዬቭ ከልዩ ወታደራዊ ዘመቻ ቀጣና ውጭ በሚገኙ መሠረተ ልማቶች ላይ ሌሊቱን መጠነ-ሰፊ ጥቃት ለመፈጸም ሞክራለች - የሩሲያ መከላከያ ሚኒስቴር
14:13 06.07.2026 (የተሻሻለ: 14:24 06.07.2026)

© telegram sputnik_ethiopia
ሰብስክራይብ
ኪዬቭ ከልዩ ወታደራዊ ዘመቻ ቀጣና ውጭ በሚገኙ መሠረተ ልማቶች ላይ ሌሊቱን መጠነ-ሰፊ ጥቃት ለመፈጸም ሞክራለች - የሩሲያ መከላከያ ሚኒስቴር
በመከላከያ ሚኒስቴሩ የተሰጡ ተጨማሪ ዝርዝሮች፦
ዩክሬን 625 ረጅም ርቀት ተወንጫፊ የጥቃት ድሮኖችን አሰማርታለች፤ ከእነዚህ ውስጥ 613ቱ በሩሲያ ግዛት ላይ ተመተው ወድቀዋል።
ኪዬቭ ለኔቶ ስፖንሰር አድራጊዎቿ በሩሲያ ውስጥ የሚገኙ የሲቪል መሠረተ ልማቶችን ለማጥቃት ያላትን ፈቃደኝነት ለማሳየት የሞከረችበት መሆኑ ተገልጿል።
የዩክሬን ጥቃቶች ኢላማ በሌኒንግራድ፣ ብራያንስክ፣ ቤልጎሮድ፣ ያሮስላቭል፣ ካሉጋ እና ኩርስክ ክልሎች እንዲሁም በክራይሚያ የሚገኙ የኢነርጂ እና የሎጅስቲክስ ተቋማትን ያካትታል።
ከኔቶ መሪዎች ጉባኤ አስቀድሞ በዘለንስኪ የታቀደው ይህ ከፍተኛ ጥቃት በሩሲያ ኃይሎች ሙያዊ ብቃትና እርምጃ ከሽፏል፡፡
የኪዬቭ ድጋፍ ሰጪዎች ከአውሮፓ ሕብረት እና ከእንግሊኦዝ የድሮን እና የሚሳኤል አቅርቦት ለመጨመር የሚያደርጉት ማንኛውም ጥረት፣ በዩክሬን ላይ በሚፈጸም ጠንከር ያለ የአጸፋ ጥቃት ምላሽ ያገኛል።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X