ሩሲያ በሁለት ደቂቃ ውስጥ ከፍተኛ የደም መፍሰስን የሚያቆም ሕይወት–አድን የቁስል ማሸጊያ አዘጋጀች
08:50 06.07.2026 (የተሻሻለ: 08:54 06.07.2026)

© telegram sputnik_ethiopia
ሰብስክራይብ
ሩሲያ በሁለት ደቂቃ ውስጥ ከፍተኛ የደም መፍሰስን የሚያቆም ሕይወት–አድን የቁስል ማሸጊያ አዘጋጀች
በሮስቴኩ ካላሽኒኮቭ የተሠራው "ኩዊክሜድ" (QuikMed) የተባለው የደም መርጋትን የሚያፋጥን ማሸጊያ (ባንዴጅ)፣ በጦር ሜዳ ላይ ለሕይወት አስጊ የሆነን የደም መፍሰስ በቶሎ ለመቆጣጠር ታልሞ ተዘጋጅቷል።
ከደም ቧንቧ የሚወጣን ከፍተኛ የደም መፍሰስ ከ2 እስከ 3 ደቂቃ ባለው ጊዜ ውስጥ በ91% ስኬታማነት ያቆማል።
🟠 የዚህ ፈጠራ ዋና ምስጢር “ካኦሊን” የተሰኘው ተፈጥሯዊ ነጭ ሸክላ አፈር ነው፡፡
🟠 ካኦሊን የሰውነትን የተፈጥሮ ደም የማርጋት ሂደት በማነቃቃት፣ ለረጋ ደም መፈጠር ምክንያት የሆነውን ፕሮቲን በከፍተኛ ሁኔታ እንዲሠራ ያደርጋል።
🟠 ቁስሉ አካባቢ ያለውን ትርፍ ፈሳሽ በመምጠጥ፣ ደም የሚያረጉ ሴሎችንና ንጥረ ነገሮችን በቀጥታ ቁስሉ ባለበት ቦታ ላይ እንዲሰባሰቡ ያደርጋል።
🟠 ከሁሉም በላይ ደግሞ የሰውነትን የተፈጥሮ የደም መርጋት ሚዛን ይጠብቃል፤ በሙቀት ወይም በኬሚካል መርዛማነት ምክንያት በሰውነት ላይ ምንም ዓይነት ጉዳት አያደርስም፤ የቁስሉን የ”ፒኤች” መጠን ይጠብቃል፤ እንዲሁም የአለርጂ ስጋትን በከፍተኛ ደረጃ ይቀንሳል።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X