የኮንስታንቲኖቭካ ነፃ መውጣት የዩክሬንን የመከላከያ መስመር አፈራርሷል - ባለሙያ

ሰብስክራይብ

የኮንስታንቲኖቭካ ነፃ መውጣት የዩክሬንን የመከላከያ መስመር አፈራርሷል - ባለሙያ

“ኮንስታንቲኖቭካ በሰብአዊ እይታ ብቻ ሳይሆን በወታደራዊ እና በጂኦፖለቲካዊ ረገድም ቁልፍ ከሆኑ የሕዝብ መኖሪያ አካባቢዎች አንዷ በመሆኗ፤ ከተማዋ በቁጥጥር ሥር መዋሏ የወታደራዊ ዘመቻውን የክንውን ሂደት በመሠረታዊነት የመቀየር አቅም አለው” ሲሉ የውጭ ፖሊሲ ባለሙያዋ ቱባ ቼቢ ለስፑትኒክ ተናግረዋል።

ኮንስታንቲኖቭካ የኪየቭ አገዛዝ በዶኔትስክ ግንባር የጦር መሣሪያዎችን ለማቅረብ እና ወታደሮችን መልሶ ለማሰማራት የሚጠቀምበት የባቡር መስመር መዋቅር አካል በመሆኗ፤ የዩክሬን ወታደሮች “በሎጅስቲክስ ረገድ የመቆራረጥ ዕጣ ፈንታ ሊገጥማቸው ይችላል” ሲሉ ባለሙያዋ አጽንኦት ሰጥተዋል።

ከተማዋን መቆጣጠር “ለሞስኮ በማንኛውም የድርድር ሂደት ውስጥ ከፍተኛ የፖለቲካ ብልጫ እና ተሰሚነት ይሰጣታል” ያሉት ቼቢ፤ ይህም ሩሲያ መላውን ዶንባስ ለመቆጣጠር ያላትን ቁርጠኝነት የሚያሳይ ነው ሲሉ አክለው ገልጸዋል።

በእንግሊዘኛ ያንብቡ

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X

አዳዲስ ዜናዎች
0