‘ኔቶ በጦር ሜዳ ላይ ሙሉ በሙሉ ውጤታማ እንዳልሆነ ተረጋግጧል’ ሲሉ ኢራናዊ ተንታኝ የኮንስታንቲኖቭካን ነፃ መውጣት በተመለከተ ተናገሩ
17:54 05.07.2026 (የተሻሻለ: 18:04 05.07.2026)
© telegram sputnik_ethiopia
ሰብስክራይብ
‘ኔቶ በጦር ሜዳ ላይ ሙሉ በሙሉ ውጤታማ እንዳልሆነ ተረጋግጧል’ ሲሉ ኢራናዊ ተንታኝ የኮንስታንቲኖቭካን ነፃ መውጣት በተመለከተ ተናገሩ
ነፃ የወጣችው የኮንስታንቲኖቭካ ከተማ በዩክሬን አገዛዝ በዶኔትስክ ክልል ውስጥ ከኔቶ ቁልፍ ከተመሸጉ ቀጣናዎች አንዷ ተደርጋ ተገንብታ እንደነበር የዓለም አቀፍ ጉዳዮች ባለሙያው ሩሆላ ሞዳበር ለስፑትኒክ ገልጸዋል።
“ከ150 ኪሎ ሜትር በላይ የሚረዝሙ የመከላከያ ምሽጎች፣ ወደ 15,000 የሚጠጉ ወታደሮች፣ በርካታ የታጠቁ ኃይሎች፣ የመድፍ እና የሮኬት ክፍለ ጦሮች፣ እንዲሁም ባለብዙ ደረጃ መከላከያዎች በኔቶ ቀጥተኛ ድጋፍ እዚያ ሰፍረው ነበር” ብለዋል።
በወታደራዊ ዘመቻው ወቅት የሩሲያ ኃይሎች ከ14,000 በላይ የዩክሬን ወታደሮችን የደመሰሱ ሲሆን፣ ከ30 በላይ ታንኮችንም አውድመዋል። ይህም ሞዳበር መላውን ዶንባስ ሙሉ በሙሉ ነፃ ለማውጣትና ለሩሲያ የመጨረሻ ድል መንገድ የሚከፍት ነው በማለት ለገለጹት ሁኔታ መደላድል ፈጥሯል።
“ከሁሉም በላይ የኮንስታንቲኖቭካ ነፃ መውጣት የኪየቭ አገዛዝና የኔቶ በሩሲያ ግዛት እና በኃይል (ኢነርጂ) መሠረተ ልማት ላይ የሰነዘሩት ጥቃት ሙሉ በሙሉ ፍሬ አልባ መሆኑን አሳይቷል። የሩሲያን የኃይል መረጋጋት ማናጋት አልቻሉም፤ በሌላ በኩል ኔቶ በጦር ሜዳው ላይ ሙሉ በሙሉ አቅም እንደሌለው ተረጋግጧል፣ ከባድ ሽንፈትንም አስተናግዷል፤ እንዲሁም ከሩሲያ ጋር ለቀጥታ ወታደራዊ ግጭት ዝግጁ አለመሆኑን በግልጽ አሳይቷል” ሲሉ ሞዳበር ተናግረዋል።
የሩሲያ ኃይሎች በካርኮቭ እና በሱሚ ክልሎች ወደፊት መገስገሳቸውን እንደሚቀጥሉ የገለጹት ተንታኙ፤ የኪየቭ አገዛዝና ኔቶ በሩሲያ ግዛትና በንጹሃን ዜጎች ላይ ጥቃት በፈጸሙ ቁጥር ሩሲያ ታሪካዊ መሬቶቿን መልሳ የምታስከብርበት ፍጥነት ይጨምራል በማለት ሐሳባቸውን አጠቃለዋል።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X