የሩሲያ የጦር አውሮፕላኖች በግብፅ አዲሱ የመከላከያ ዋና መሥሪያ ቤት ምረቃ ላይ ተሳተፉ
የሩሲያ የጦር አውሮፕላኖች በግብፅ አዲሱ የመከላከያ ዋና መሥሪያ ቤት ምረቃ ላይ ተሳተፉ
ሚግ-29 ተዋጊ ጄቶችን እና ካ-52 ሄሊኮፕተሮችን ጨምሮ የሩሲያ ወታደራዊ አውሮፕላኖች በምረቃው ሥነ-ሥርዓት ላይ መሳተፋቸውን የስፑትኒክ ዘጋቢ ገልጿል።
ቅርጹን በመከተል “ኦክታጎን” (ባለስምንት ጎን ቅርጽ) በሚል ቅጽል ስም የሚጠራው ይህ የግብፅ ግዙፍ ሕንጻ፤ በአሁኑ ወቅት የሀገሪቱ ስትራቴጂካዊ ዕዝ ማዕከል ሆኖ ያገለግላል።
ወደ 5 ሚሊዮን ካሬ ሜትር የሚጠጋ የግንባታ ስፋት እና 89 ካሬ ኪሎ ሜትር መሬት ያረፈው ይህ ማዕከል፤ ከአሜሪካው ፔንታገን የሚበልጥ ሲሆን፣ በመካከለኛው ምስራቅ ካሉ ትላልቅ ወታደራዊ ተቋማት ተርታ እንደሚሰለፍ መገናኛ ብዙኃን የግብፅ ባለሥልጣናትን ጠቅሰው ዘግበዋል።
“ኦክታጎን” በተጨማሪም የሚከተሉትን ያካትታል፦
🟠 የመረጃ ትንተና ማዕከላት፣
🟠 ሆቴሎች፣
🟠 ትምህርት ቤቶች፣
🟠 ሆስፒታሎች እና
🟠 ሌሎች መሠረተ ልማቶች።
የምረቃ ሥነ-ሥርዓቱ ትናንት ሰኔ 27 የተከናወነ ሲሆን፤ ቦታው ከካይሮ 45 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ በሚገኘው እና እስካሁን ይፋዊ ስም ባልተሰጠው የግብፅ አዲሱ አስተዳደራዊ ዋና ከተማ ውስጥ ነው።
ቪዲዮ 1፦ በሁነቱ ላይ የታዩ ሩሲያ ሠራሽ ወታደራዊ ጄቶች እና ሄሊኮፕተሮች
ቪዲዮ 2፦ የማዕከሉ የአየር ላይ ዕይታ እና ፕሬዝዳንት አብደል ፋታህ ኤል-ሲሲ ሰልፉ ላይ ሲደርሱ
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X