በኢትዮጵያ አዲስ የተገኘው የ‘ፓራኢባ’ ማዕድን የዓለም የከበሩ ድንጋዮች ኢንዱስትሪን ቀልብ ሳበ

ሰብስክራይብ

በኢትዮጵያ አዲስ የተገኘው የ‘ፓራኢባ’ ማዕድን የዓለም የከበሩ ድንጋዮች ኢንዱስትሪን ቀልብ ሳበ

የስዊስ የጂሞሎጂ ኢንስቲትዩት በኢትዮጵያ ውስጥ አዲስ የመዳብ ይዘት ያለው የቱርማሊን ክምችት ስለመገኘቱ አስተማማኝ የንግድ ሪፖርቶች እንደደረሱት አስታውቋል።

ይህ ደማቅ ሰማያዊ እና አረንጓዴ ቀለም ያለው እንዲሁም “ኒዮን” ወይም "ኤሌክትሪክ" በመባል የሚታወቀው እጅግ ውድ የከበረ ድንጋይ፤ ለመጀመሪያ ጊዜ በ1980ዎቹ በብራዚል ፓራኢባ ግዛት የተገኘ ሲሆን፣ በኋላም በናይጄሪያ እና ሞዛምቢክ መገኘቱ ይታወሳል።

ተቋሙ ለምርመራ ከቀረቡለት ማዕድናት መካከል የአንዳንዶቹን መገኛ መለየት ፈታኝ እንደሆነበት ጠቅሶ፣ እነዚህ ድንጋዮች ከኢትዮጵያ የተገኙ ሊሆኑ እንደሚችሉ ጠቁሟል።

በአሁኑ ወቅት የኢትዮጵያውን ማዕድን ለይቶ ለማወቅና ከሌሎች ሀገራት ክምችት ጋር ያለውን ልዩነት በግልጽ ለመወሰን የሚያስችሉ የምርምር እና የትንተና ሥራዎች እየተከናወኑ መሆኑን ኢንስቲትዩቱ አስታውቋል።

ከማኅበራዊ ሚዲያ የተገኘ ቪዲዮ

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X

አዳዲስ ዜናዎች
0