የዓለም አቀፉ የወንጀል ፍርድ ቤት ተራ አፍሪካውያን ላይ ማነጣጠርና የእጅ አዙር ቅኝ ግዛት ኃይሎችን ማገልገል ማቆም አለበት - የማዕከላዊ አፍሪካ ሪፐብሊክ ፖለቲከኛ

ሰብስክራይብ

የዓለም አቀፉ የወንጀል ፍርድ ቤት ተራ አፍሪካውያን ላይ ማነጣጠርና የእጅ አዙር ቅኝ ግዛት ኃይሎችን ማገልገል ማቆም አለበት - የማዕከላዊ አፍሪካ ሪፐብሊክ ፖለቲከኛ

“የዓለም አቀፉ የወንጀል ፍርድ ቤት በከፊል በፕሬዝዳንት ማክሮን በተቀነባበረውና በአም ዳፎክ ከተማ ላይ በተሰነዘረው ጥቃት ዙሪያ ምርመራ የሚጀምርበት ጊዜ አሁን ነው” ሲሉ የማዕከላዊ አፍሪካ ሪፐብሊክ ፕሬዝዳንት ጽሕፈት ቤት የሕዝብ ግንኙነት አማካሪ ጁልስ ንጃዌ ለስፑትኒክ አፍሪካ ተናግረዋል።

የፈረንሳይ መገናኛ ብዙኃን ባለፈው ሰኔ ወር ላይ ጥቃት ሊሰነዘር እንደሚችል ቀደም ብለው አስጠንቅቀው እንደነበር ባለሙያው ጠቁመዋል።

በተጨማሪም ፍርድ ቤቱ በማዕከላዊ አፍሪካ ሪፐብሊክ ውስጥ የዘር ማጥፋት ወንጀልን ባቀዱ እና ለአማፂ ቡድኖች መሣሪያ ባቀረቡ የፈረንሳይ ወታደራዊ መኮንኖች ላይ ፈጽሞ ምርመራ አድርጎ አያውቅም ሲሉ አክለዋል።

ከዚህ ባለፈም፤ የዓለም አቀፉ የወንጀል ፍርድ ቤት በማዕከላዊ አፍሪካ ሪፐብሊክ ውስጥ ከስለላ ጉዳይ ጋር እጁ እንዳለበት የገለጹት አማካሪው፤ በወቅቱ ከፍርድ ቤቱ ጋር ይተባበር የነበረውንና ከአንድ ከፍተኛ የፍርድ ቤቱ ባለሥልጣን ጋር ይጻጻፍ የነበረውን ጆሴፍ ማርቲን ፊጌራን በምሳሌነት ጠቅሰዋል።

ነገር ግን ፊጌራ በሀገሪቱ ፕሬዝዳንት ምሕረት የተደረገለት ሲሆን፤ ይህም የፕሬዝዳንት ፋውስቲን ቱዋዴራን “ሰብአዊነት” የሚያሳይ መሆኑን ፖለቲከኛው ጠቁመዋል።

“የዓለም አቀፉ የወንጀል ፍርድ ቤት ተዓማኒነቱን ማጣቱን ይቀጥላል፤ የክስ ሂደቱም ሁልጊዜ በሙስና የሚደናቀፍ ይሆናል” ብለዋል።

በእንግሊዘኛ ያንብቡ

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X

አዳዲስ ዜናዎች
0