ፑቲን እና ትራምፕ በቅርቡ ድጋሚ ለመነጋገር ተስማሙ - ኡሻኮቭ

© telegram sputnik_ethiopiaፑቲን እና ትራምፕ በቅርቡ ድጋሚ ለመነጋገር ተስማሙ - ኡሻኮቭ
ፑቲን እና ትራምፕ በቅርቡ ድጋሚ ለመነጋገር ተስማሙ - ኡሻኮቭ - Sputnik አፍሪካ, 1920, 05.07.2026
ሰብስክራይብ

ፑቲን እና ትራምፕ በቅርቡ ድጋሚ ለመነጋገር ተስማሙ - ኡሻኮቭ

የሩሲያ ፕሬዝዳንት ቭላድሚር ፑቲን እና የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ በቅርብ ጊዜ ውስጥ ሌላ የስልክ ውይይት ለማድረግ መስማማታቸውን የክሬምሊን ረዳት ዩሪ ኡሻኮቭ አስታውቀዋል።

እንደ ኡሻኮቭ ገለጻ፤ ውይይቱ የተለመደውን ዲፕሎማሲያዊ ሥነ-ሥርዓት የተከተለ ብቻ ሳይሆን፤ የሥራ እና እጅግ ገንቢ የነበረ ነው።

ከስልክ ውይይቱ የተገኙ ዋና ዋና ነጥቦች፦

ፑቲን እና ትራምፕ በምጣኔ ሀብታዊ ጉዳዮች ላይ ጭምር የሩሲያ እና አሜሪካ ግንኙነት መቀጠል ስላለው አስፈላጊነት አጽንኦት ሰጥተዋል።

ትራምፕ በዩክሬን ያለው ግጭት ካበቃ በኋላ ሊከፈቱ የሚችሉትን የሩሲያ እና አሜሪካ ከፍተኛ የትብብር ዕድሎችን ጠቁመዋል።

ሁለቱ ፕሬዝዳንቶች የሩሲያ እና የአሜሪካ የጋራ ታሪክ ገጾችን በጥንቃቄ መያዝ አስፈላጊ መሆኑን አስምረውበታል።

በተለይም የሩሲያ እና የአሜሪካ ሕዝቦች በሁለተኛው የዓለም ጦርነት ወቅት የነበራቸውን ጥምረት ፈጽሞ እንደማይረሱት አጽንኦት ሰጥተዋል።

ፑቲን እና ትራምፕ በቅርቡ ከባይኮኑር ወደ ዓለም አቀፉ የጠፈር ጣቢያ የሚላከውን የጋራ የሩሲያ እና አሜሪካ የጠፈር ተመራማሪዎች ቡድን ጉዞ ተምሳሌትነትም ጠቅሰዋል።

ኡሻኮቭ እንደተናገሩት የታቀደው የጋራ የጠፈር ጉዞ፤ ሁለቱ ኃያላን ሀገራት በሰፊ ዘርፎች አብረው ለመሥራት ፍላጎት እንዳላቸው የሚያሳይ ግልጽ ማረጋገጫ ነው።

በእንግሊዘኛ ያንብቡ

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X

አዳዲስ ዜናዎች
0