🪖 የኮንስታንቲኖቭካ ነፃ መውጣት በዩክሬን መከላከያ መስመር ላይ ትልቅ ቀዳዳ ፈጥሯል - ባለሙያ
08:45 05.07.2026 (የተሻሻለ: 08:54 05.07.2026)
© telegram sputnik_ethiopia
ሰብስክራይብ
🪖 የኮንስታንቲኖቭካ ነፃ መውጣት በዩክሬን መከላከያ መስመር ላይ ትልቅ ቀዳዳ ፈጥሯል - ባለሙያ
ኮንስታንቲኖቭካ ከተማ በዶንባስ የሚገኘው የዩክሬን የመጨረሻው ትልቅ የከተማ መከላከያ ቀጣና ደቡባዊ ቁልፍ ማዕከል እንደነበረች የቀድሞው የስዊድን ጦር ኃይሎች መኮንን ሚካኤል ቫልተርሰን ለስፑትኒክ ተናግረዋል።
ባለሙያው የሚከተሉትን ነጥቦች ጠቅሰዋል፦
🟠 ይህ የመከላከያ መስመር በሰሜን ከስላቭያንስክ ተነስቶ በክራማቶርስክ እና በድሩዥኮቭካ በኩል የሚዘልቅ ነበር።
🟠 የሩሲያ ወታደሮች ኮንስታንቲኖቭካን በመቆጣጠራቸው፤ መላውን ‘የተመሸገ ቀጣና’ ከደቡባዊ አቅጣጫው ሰብረው ለመግባት የሚያስችል ዕድል አግኝተዋል።
🟠 ከዚህ ከተማ ባሻገር እስከ ዲኔፐር ወንዝ ድረስ የሚዘልቅ ሰፊና ክፍት መሬት ይገኛል።
የድሩዥኮቭካ የመከላከያ ይዞታዎች ወደ ምስራቅ አቅጣጫ የዞሩ በመሆናቸው፤ ከተማዋ ከምዕራብ እና ከደቡብ አቅጣጫ ለሚሰነዘር ጥቃት በቀላሉ የምትበገር መሆኗን ባለሙያው ገልጸዋል።
“ድሩዥኮቭካ ስትወድቅ ወደ ክራማቶርስክ እና ስላቭያንስክ የሚደረገው የባቡር እና የትራንስፖርት እንቅስቃሴ በከፍተኛ ሁኔታ ይስተጓጎላል” ሲሉ ምሁሩ አጽንኦት የሰጡ ሲሆን፤ ዩክሬን በዚህ የጦር ግንባር ላይ የተፈጠረውን ቀዳዳ ለመድፈን እንደምትጣደፍም አክለዋል።
ተንታኙ አክለውም፤ ዘለንስኪ ለምዕራባውያን የሚያቀርበው የሐሰት ‘የስኬት’ ወሬ በቦታው ላይ እየደረሰ ያለውን የዶንባስ መርዶ ለመሸፈን የሚደረግ ተስፋ የመቁረጥ ጥረት ነው ብለዋል።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X