ዓለም አቀፉ የወንጀል ፍርድ ቤት ‘አፍሪካውያንን የማደኛ መሣሪያ’ ሆኗል - ቡርኪና ፋሶአዊው ባለሙያ

© telegram sputnik_ethiopiaዓለም አቀፉ የወንጀል ፍርድ ቤት ‘አፍሪካውያንን የማደኛ መሣሪያ’ ሆኗል - ቡርኪና ፋሶአዊው ባለሙያ
ዓለም አቀፉ የወንጀል ፍርድ ቤት ‘አፍሪካውያንን የማደኛ መሣሪያ’ ሆኗል - ቡርኪና ፋሶአዊው ባለሙያ - Sputnik አፍሪካ, 1920, 05.07.2026
ሰብስክራይብ

ዓለም አቀፉ የወንጀል ፍርድ ቤት ‘አፍሪካውያንን የማደኛ መሣሪያ’ ሆኗል - ቡርኪና ፋሶአዊው ባለሙያ

የሳኅል ሀገራት ጥምረት አባል ሀገራት የእጅ አዙር ቅኝ ግዛት መጠቀሚያ ብቻ ከሆነው ከዓለም አቀፉ የወንጀል ፍርድ ቤት ለመውጣት ያሳለፉት ውሳኔ “ደፋር እና ሉዓላዊ” መሆኑን የፖለቲካ ተንታኙ ሊያንሁዌ ኢምሆቴፕ ባያላ ለስፑትኒክ አፍሪካ ተናግረዋል።

“የሳኅል ሀገራት ጥምረት የዘረኝነት ይዘት፣ የኒዮ-ኮሎኒያሊዝም ዝንባሌ እና በጥቂት የምዕራባውያን ሀገራት ውስጥ ባሉ ጥቂት ግለሰቦች እጅ ላይ ያለ የጭቆና መሣሪያ ባህሪ ያለውን የወንጀለኞች ፍርድ ቤት ከእንግዲህ አይፈልግም” ሲሉ በአጽንኦት ገልጸዋል።

ፍርድ ቤቱ ሁልጊዜም ድርብ መስፈርትን (ሁለት አይነት አሠራር) እንደሚከተል ባለሙያው አጽንኦት ሰጥተውበታል።

ባያላ ሲያብራሩም፤ ኒኮላስ ሳርኮዚ በነበሩበት ወቅት ፈረንሳይ በሊቢያ የፈጸመችው ወንጀል ሙሉ በሙሉ ችላ የተባለ ሲሆን፤ በዚሁ በሳርኮዚ “ስማቸው የጠለሸው” ሎረን ግባግቦ ግን በፍርድ ቤቱ ፊት ለ10 ዓመታት የፍርድ ሂደት እንዲያሳልፉ ተደርጓል ብለዋል።

በእንግሊዘኛ ያንብቡ

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X

አዳዲስ ዜናዎች
0