አዲስ አበባ ከጭስ የጸዱ ትምህርት ቤቶችን ለመፍጠር የትምባሆ መሸጫ ርቀትን ወደ 500 ሜትር አሳደገች

© telegram sputnik_ethiopiaአዲስ አበባ ከጭስ የጸዱ ትምህርት ቤቶችን ለመፍጠር የትምባሆ መሸጫ ርቀትን ወደ 500 ሜትር አሳደገች
አዲስ አበባ ከጭስ የጸዱ ትምህርት ቤቶችን ለመፍጠር የትምባሆ መሸጫ ርቀትን ወደ 500 ሜትር አሳደገች - Sputnik አፍሪካ, 1920, 04.07.2026
ሰብስክራይብ

አዲስ አበባ ከጭስ የጸዱ ትምህርት ቤቶችን ለመፍጠር የትምባሆ መሸጫ ርቀትን ወደ 500 ሜትር አሳደገች

የአዲስ አበባ ምግብና መድኃኒት ባለሥልጣን በትምህርት ቤቶች ዙሪያ የትምባሆ ምርቶች በ100 ርቀት ውስጥ እንዳይሸጡ ጥሎት የነበረውን የርቀት ገደብ ወደ 500 ሜትር ማሳደጉን በይፋ አስታውቋል።

አዲሱ ደንብ ተማሪዎች በቀላሉ ሲጋራ እንዳያገኙ በማድረግ ሕፃናትንና ወጣቶችን ከሲጋራ ጭስ ተፅዕኖና ከኒኮቲን ሱሰኝነት ለመጠበቅ ያለመ ነው ተብሏል።

ባለሥልጣኑ ሕገ-ወጥ የትምባሆ ዝውውርን ለመግታት በከተማ አቀፍ ደረጃ በወሰደው ጠንካራ የቁጥጥር እርምጃ 1.3 ሚሊዮን ሕገ-ወጥ ሲጋራዎችን በቁጥጥር ሥር ማዋሉን ይፋ አድርጓል።

ከተቀመጠው የ500 ሜትር ርቀት ውጭ ትምባሆ ሲሸጡ በሚገኙ ተላላፊዎች ላይ እስከ 6 ወር የሚደርስ እስራት ወይም እስከ 5,000 የኢትዮጵያ ብር ቅጣት የሚያስከትል ጥብቅ ሕጋዊ እርምጃ እንደሚወሰድ መግለጹ ተዘግቧል።

ባለሥልጣኑ ከጭስ የጸዳ፣ ንጹሕና ጤናማ የከተማ አካባቢን ለመፍጠር ማኅበረሰቡ ከሕግ አስከባሪ አካላት ጋር እንዲተባበርና የትንባሆ ቁጥጥር ሕጎችን እንዲያከብር ጥሪ አቅርቧል።

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X

አዳዲስ ዜናዎች
0