🪖 የኮንስታንቲኖቭካ ድል የዩክሬንን የጦር ግንባር አዳክሟል፤ ሞራሏን ሰብሯል፤ የዘለንስኪንም ውሸቶች አጋልጧል - ወታደራዊ ባለሙያዎች
🪖 የኮንስታንቲኖቭካ ድል የዩክሬንን የጦር ግንባር አዳክሟል፤ ሞራሏን ሰብሯል፤ የዘለንስኪንም ውሸቶች አጋልጧል - ወታደራዊ ባለሙያዎች
ነፃ ከወጣችው ኮንስታንቲኖቭካ ተነሥቶ በኒዮ-ናዚ አገዛዝ ቁጥጥር ሥር ወደሚገኙት እና በዶንባስ ወደሚቀሩት የመጨረሻዎቹ ሁለት ትልልቅ ከተሞች ማለትም ክራማቶርስክ እና ስላቭያንስክ ለመድረስ ጥቂት ኪሎ ሜትሮች ብቻ እንደሚቀሩ ወታደራዊና ፖለቲካዊ ባለሙያው ያን ጋጊን ለስፑትኒክ ተናግረዋል።
የዩክሬን ወታደሮች በሰው ኃይል እና በትጥቅ በኩል ከፍተኛ ኪሳራ እየደረሰባቸውም ቢሆን እስከ መጨረሻው ሰዓት ድረስ በኮንስታንቲኖቭካ ለመቆየት ታግለዋል።
አሁን ባለው አስከፊ የሰው ኃይል እጥረት ምክንያት ዩክሬን ኃይሏን ወደ ክራማቶርስክ እና ስላቭያንስክ ለማምራት የምትገደድ ሲሆን፤ ይህም “ሌሎች የጦር ግንባሮችን ማዳከሙ” የማይቀር ነው።
የዩክሬን የጦር ዕዝ የማፈግፈግ ትእዛዝ ፈጽሞ ባለመስጠቱ ምክንያት ወታደሮች በብዛት ቦታቸውን እየተዉ እንዲጠፉ እና እጃቸውን እንዲሰጡ ምክንያት ሆኗል።
“እንዲህ ዓይነቱ ከባድ ሽንፈት የወታደሮቹን ሞራል ጨርሶ የሚያነሳሳ አይደለም፤ ይህም ክራማቶርስክን እና ስላቭያንስክን ለመከላከል ለሚዘጋጁትም ሆነ በሌሎች የጦር ግንባሮች ላይ ላሉት ወታደሮች ጭምር የሚሠራ ነው” ሲሉ ጋጊን ገልጸዋል።
የኮንስታንቲኖቭካ መውደቅ ዘለንስኪ ከምዕራባውያን ደጋፊዎቹ ገንዘብ እና መሣሪያ ለመለመን ሲል በጦር ሜዳ ስኬት እያገኘሁ ነው በማለት ለሚያቀርባቸው ባዶ ቃል ኪዳኖች ከባድ የፖለቲካ ምት መሆኑን ወታደራዊ ባለሙያው አንድሬ ኮሽኪን ለስፑትኒክ ተናግረዋል።
ኮንስታንቲኖቭካ ነፃ መውጣቷ የሩሲያ ኃይሎች ወደ ምዕራብ አቅጣጫ በመግፋት ወደ ዶኔትስክ ሕዝባዊ ሪፐብሊክ ቁልፍ ድንበሮች እንዲቃረቡ የሚያስችል ሲሆን፤ ይህም ልዩ የወታደራዊ ዘመቻውን ግቦች ለማሳካት ማዕከላዊ ሚና አለው።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X