ኢትዮጵያ በ8.2 ቢሊዮን ብር ወጪ 150 የኤሌክትሪክ አውቶቡሶችን ልትገዛ መሆኑ ተዘገበ
17:45 04.07.2026 (የተሻሻለ: 17:54 04.07.2026)
© telegram sputnik_ethiopia
ሰብስክራይብ
ኢትዮጵያ በ8.2 ቢሊዮን ብር ወጪ 150 የኤሌክትሪክ አውቶቡሶችን ልትገዛ መሆኑ ተዘገበ
የኢትዮጵያ የብዙሃን ትራንስፖርት አገልግሎት ለከተማ የሕዝብ ትራንስፖርት፣ ለቱሪዝም አገልግሎት እና ለቀጣይ ቀጣናዊ የድንበር ተሻጋሪ ጉዞዎች የሚውሉ እያንዳንዳቸው 55 ሚሊዮን ብር ገደማ የሚገመቱ 150 የኤሌክትሪክ አውቶቡሶችን ለመግዛት እየተዘጋጀ መሆኑን አስታውቋል።
ተቋሙ የግዢውን ግማሽ ወጪ በያዝነው የበጀት ዓመት የሚከፍል ሲሆን፤ ቀሪውን 50 በመቶ ደግሞ በቀጣዩ የበጀት ዓመት የመጀመሪያ ስድስት ወራት ውስጥ ለማጠናቀቅ ማቀዱ ተገልጿል።
ግዢው በተቋሙ አመራር የጸደቀ ሲሆን በአሁኑ ወቅት የቦርድ ድጋፍን እየጠበቀ እንደሚገኝ የተቋሙ ተጠባባቂ ዋና ዳይሬክተር ታደዎስ ለራ ለሀገር ውስጥ ሚዲያ ተናግረዋል።
የኤሌክትሪክ አውቶቡሶቹ የነዳጅ ወጪን በከፍተኛ ሁኔታ እንደሚቀንሱና በከተማ ትራንስፖርት ላይ ያለውን እጥረት ከመቅረፍ ባለፈ ወደ ቱሪስት መዳረሻዎች እና ወደ ጎረቤት አገራት ለሚደረጉ የየብሥ ላይ የጉዞ መስመሮች አገልግሎት እንደሚሰጡ ተመላክቷል።
በአንድ ዓመት በፊት የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ወደ ሥራ ያስገባቸው የኤሌክትሪክ አውቶቡሶች
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X