የኢራን እና አሜሪካ የመግባቢያ ስምምነት ለከባድ የኒውክሌር ድርድር መነሻ ይሆናል - የሩሲያ ደህንነት ምክር ቤት ምክትል ኃላፊ
15:48 04.07.2026 (የተሻሻለ: 15:54 04.07.2026)
© telegram sputnik_ethiopia
ሰብስክራይብ
የኢራን እና አሜሪካ የመግባቢያ ስምምነት ለከባድ የኒውክሌር ድርድር መነሻ ይሆናል - የሩሲያ ደህንነት ምክር ቤት ምክትል ኃላፊ
ድርድር ማድረግ ምንም ዓይነት ውይይት ከመጥፋቱ የተሻለ ቢሆንም፤ ወደ መጨረሻው ስምምነት የሚያደርሰው መንገድ ግን “እጅግ አስቸጋሪ” እንደሚሆን ዲሚትሪ መድቬዴቭ በቴህራን ባደረጉት ጉብኝት ወቅት ተናግረዋል። መድቬዴቭ በጉብኝታቸው የፕሬዝዳንት ፑቲንን የሀዘን መግለጫ በአያቶላ ኻሜኒ የቀብር ስነ-ሥርዓት ላይ አቅርበዋል።
ከመድቬዴቭ ንግግር የተወሰዱ ዋና ዋና ነጥቦች፦
ድርድሮች አስፈላጊ ቢሆኑም፤ በአሜሪካ ያሉ በርካታ አካላት በኢራን ላይ የተጣለው ማዕቀብ እንዲነሳ እንደማይፈልጉ አስገንዝበዋል።
የሆርሙዝ ወሽመጥ ለኢራን “ከኒውክሌር መሣሪያ ያላነሰ ኃይል ያለው መሣሪያ” ሲሆን፤ የባብ ኤል-ማንደብ የባሕር ወሽመጥ ደግሞ በተጠባባቂነት የሚያገለግል “ቴርሞ-ኒውክሌር መሣሪያ” ነው ብለዋል።
ሩሲያ፣ ኢራን፣ ቻይና እና ሌሎች ሀገራት ማዕቀብ የተጣባባቸው ሀገራትን የሚያስተሳስር የጋራ መድረክ ስለሚፈጠርበት ሁኔታ መወያየት እንደሚችሉ ጠቁመዋል።
የኢራንን የኒውክሌር ጉዳይ በሰላማዊ መንገድ መፍታት የሚችሉ የውሳኔ ሐሳቦችን ሞስኮ ማቅረቧን አስታውቀዋል።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X